በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ፓቨል ካዛዴቭ

ኅዳር 24, 2022 | የታደሰው፦ ነሐሴ 21, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ስደት ቢኖርም በመንፈሳዊ ንቁ ሆኖ ለመቀጠል ቆርጧል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ስደት ቢኖርም በመንፈሳዊ ንቁ ሆኖ ለመቀጠል ቆርጧል

ነሐሴ 18, 2023 የአልታይ ግዛት ፍርድ ቤት፣ በወንድም ፓቨል ካዛዴቭ ላይ ቀደም ሲል የተላለፈውን የገደብ እስራት ወደ ሦስት ዓመት እስራት ቀይሮታል። ከፍርድ ቤት ወዲያውኑ ወደ ወህኒ ተወስዷል።

ግንቦት 29, 2023 ባርኖል፣ አልታይ ግዛት ውስጥ የሚገኘው የኢንዱስትሪያልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ፓቨል ካዛዴቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የሦስት ዓመት የገደብ እስራትም በይኖበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

የይሖዋ ሕዝቦች ፈተናዎች እያሉም ንቁና ደስተኛ ለመሆን የሚያደርጉትን ጥረት ማየት እምነት የሚያጠናክር ነው።—ማቴዎስ 5:11

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 11, 2021

    የወንጀል ምርመራው ተጀመረ

  2. ግንቦት 27, 2021

    ፖሊሶች ያስጀመሩትን “አርማጌዶን” የተሰኘ ዘመቻ ተከትሎ በኖቮኩዝኔትስክ የሚገኘው የፓቨል መኖሪያና በሌላ አካባቢ የሚኖሩ ዘመዶቹ መኖሪያ ቤት ተፈተሹ። ፓቨል እና ባለቤቱ ለምርመራ ወደ ባርኖል ተወሰዱ፤ ባርኖል ከመኖሪያ ቤታቸው 350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች። ፓቨል በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ ተሳትፈሃል ተብሎ ተከሰሰ፤ ጣቢያ እንዲያድርም ተደረገ

  3. ግንቦት 28, 2021

    ከጣቢያ ተለቀቀ፤ የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉበት

  4. ነሐሴ 12, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ