በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኢንቨር ሲዩኮቭ

ግንቦት 18, 2022 | የታደሰው፦ መጋቢት 12, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ኢንቨር ሲዩኮቭ በብርታት ተሞልቷል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ኢንቨር ሲዩኮቭ በብርታት ተሞልቷል

መጋቢት 7, 2024 በአድጄያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የማይኮፕ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ኢንቨር ሲዩኮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን በማስተላለፍ በስድስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል። ከሚያዝያ 2021 ጀምሮ ማረፊያ ቤት የነበረ ሲሆን እስራቱ በዚሁ ይቀጥላል።

የክሱ ሂደት

  1. ሚያዝያ 15, 2021

    በቪዲዮ ኮንፈረንስ ስብሰባ አድርጓል ተብሎ ተከሰሰ

  2. ሚያዝያ 16, 2021

    ፖሊሶች የኢንቨርን እና የሌሎች አራት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች ፈተሹ። ምርመራ ተደረገበት፤ ለጊዜው ጣቢያ ውስጥ እንዲቆይ ተደረገ

  3. ሚያዝያ 17, 2021

    ማረፊያ ቤት ተላከ

  4. ነሐሴ 15, 2021

    ከማይኮፕ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ ወደሚደረግበት ማረፊያ ቤት ተላከ

  5. መስከረም 13, 2021

    ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ውድ የሩሲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘ከጌታና ከታላቅ ብርታቱ ኃይል ማግኘታቸውን እንደሚቀጥሉ’ እንተማመናለን።—ኤፌሶን 6:10

a ወንድም ሲዩኮቭ አሁን የሚገኘው ማረፊያ ቤት ስለሆነ የግል አስተያየቱን ማግኘት አልተቻለም።