በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሲ ካባሮቭ

መስከረም 1, 2021| የታደሰው፦ ጥቅምት 25, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ| ወንድም አሌክሲ ካባሮቭ መጸለዩ እና የአምላክን ቃል ማንበቡ ድፍረት ሰጥቶታል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ| ወንድም አሌክሲ ካባሮቭ መጸለዩ እና የአምላክን ቃል ማንበቡ ድፍረት ሰጥቶታል

ጥቅምት 20, 2023 በፕስኮቭ ክልል የሚገኘው የፖርኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ ካባሮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን ያስተላለፈ ሲሆን የሁለት ዓመት ከስድስት ወር እስራት ፈርዶበታል። ይህ ፍርድ የተላለፈው ወንድም አሌክሲ ነፃ እንዲለቀቅ ቀደም ሲል የተላለፈውን ብይን አቃቤ ሕጉ ይግባኝ ካለ በኋላ ነው። ወንድም አሌክሲ ለፍርድ ሲቀርብ ይህ ሦስተኛ ጊዜው ነው። ከፍርድ ቤት በቀጥታ ወደ ወህኒ ተወስዷል።

ሰኔ 27, 2022 በፕስኮቭ ክልል የሚገኘው የፖርኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ ካባሮቭ ጥፋተኛ አይደለም የሚል ብይን አስተላልፏል። አሌክሲ ከተመሠረቱበት ክሶች በሙሉ ነፃ ተደርጓል።

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 26 2021 የፕስኮቭ ክልላዊ ፍርድ ቤት የአሌክሲን ይግባኝ ተመልክቷል። ክሱ በመጀመሪያው ፍርድ ቤት በሌላ ዳኛ እንዲታይ ውሳኔ አስተላልፏል። ወንድም አሌክሲ ካባሮቭ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም

  2. መስከረም 7, 2021

    በፕስኮቭ ክልል የሚገኘው የፖርኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ አሌክሲ ጥፋተኛ ነው በማለት የሦስት ዓመት የገደብ እስራት ፈረደበት።

  3. ጥቅምት 29, 2020

    የአሌክሲ ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  4. ነሐሴ 28, 2020

    አሌክሲ አማኞች ‘ስለ እምነታቸው በሚነጋገሩበት፣ መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነቡበት፣ ቅዱስ ጽሑፋዊ ጉዳዮችን በሚወያዩበትና ሃይማኖታዊ መዝሙሮችን በሚዘምሩበት’ “ሃይማኖታዊ ስብሰባ ላይ ቀናተኛ ተሳትፎ በማድረግ” ወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  5. የካቲት 7, 2020

    አሌክሲ ለሁለተኛ ጊዜ የወንጀል ምርመራ ተደረገበት። ስልኩ በ2018 ተጠልፎ እንደነበር በምርመራው ወቅት ታወቀ

  6. ጥር 31, 2020

    አሌክሲ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  7. ግንቦት 24, 2019

    አሌክሲ በፕስኮቭ ክልል ለሚገኘው የሰብዓዊ መብቶች እንባ ጠባቂ ተቋም አቤቱታውን በጽሑፍ አስገባ። አሌክሲ ወንጀለኛ ሳይሆን አማኝ እንደሆነ አበክሮ ገለጸ። እንባ ጠባቂ ተቋሙ፣ አሌክሲ እምነቱን የመያዝና የማራመድ መብት እንዳለው በመግለጽ ምላሽ ሰጠ

  8. ሚያዝያ 3, 2019

    የአሌክሲ ቤት ተፈተሸ፤ አንዳንድ ንብረቶቹ ተወረሱ፤ እንዲሁም ፖሊሶች የወንጀል ምርመራ አደረጉበት

አጭር መግለጫ

እኛም እንደ አሌክሲ፣ ይሖዋ ምንጊዜም ታማኞቹ ‘ደፋር እንዲሆኑና ልባቸው እንዲጸና’ እንደሚረዳቸው በሙሉ ልባችን እንተማመናለን።—መዝሙር 27:14