በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኒኮላይ ሳፓሮቭ ከባለቤቱ ከናታሊያ (በስተ ቀኝ) እና ከልጁ ከአናስታሲያ ጋር (በስተ ግራ)

ኅዳር 8, 2022 | የታደሰው፦ ጥር 22, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ጸሎትና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጽኑ ያደርጋሉ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ጸሎትና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጽኑ ያደርጋሉ

ጥር 17, 2024 በአድጄያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የማይኮፕ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ኒኮላይ ሳፓሮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን በማስተላለፍ የስድስት ዓመት እስራት ፈርዶበታል። ኒኮላይ ከመጋቢት 2022 ጀምሮ ማረፊያ ቤት የቆየ ሲሆን አሁንም እንደታሰረ ይቆያል።

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 22, 2022

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  2. መጋቢት 23, 2022

    ኒኮላይ ከባለቤቱና ከልጁ ጋር አየር ማረፊያ ውስጥ ሳለ በቁጥጥር ሥር ዋለ። ፖሊሶች ከመረመሩት በኋላ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አስተባብረሃል ብለው ከሰሱት። ከዚያም ወደ ጣቢያ ተወሰደ። ትንሽ ቆይቶም ቤቱ ተፈተሸ

  3. መጋቢት 24, 2022

    ኒኮላይ ወደ ማረፊያ ቤት ተዛወረ

  4. ግንቦት 19, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ከኒኮላይ ቤተሰብ ተሞክሮ እንደምንማረው ይሖዋ አገልጋዮቹ ‘እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትን ጩኸት’ ሁልጊዜም ይሰማል።—መዝሙር 119:147

a ይህ ዜና በተዘጋጀበት ወቅት ወንድም ኒኮላይ ማረፊያ ቤት በመሆኑ የእሱን አስተያየት ማግኘት አልተቻለም።