በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዳኒል ሱቮሮቭ

ታኅሣሥ 16, 2022 | የታደሰው፦ ሰኔ 20, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ፈተናው ባያቆምም ደስተኛ ነው

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ፈተናው ባያቆምም ደስተኛ ነው

ሰኔ 20, 2023 የሶቺ ማዕከላዊ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ዳኒል ሱቮሮቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል፤ የስድስት ዓመት እስራትም በይኖበታል። ዳኒል ከነሐሴ 18, 2021 አንስቶ በእስር ላይ ነበር፤ የእስራት ፍርዱም በዚሁ ይጸናል።

አጭር መግለጫ

እኛም ራሳችንን በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች እናስጠምድ፤ ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድናም እናጠናክር፤ እንዲህ ካደረግን ምንም ይምጣ ምን ደስተኛ ሆነን መቀጠል እንችላለን።—መዝሙር 16:11

የክሱ ሂደት

  1. ነሐሴ 13, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት፤ ለመጽሐፍ ቅዱስ ፍላጎት ያለው መስሎ የቀረበ አንድ ሰው ለፖሊሶች በሰጠው ቃል ላይ ነው ክሱ የተመሠረተው

  2. ነሐሴ 18, 2021

    ቤቱ ተፈተሸ። ከዚያም ተይዞ ወደ ጣቢያ ተወሰደ

  3. ነሐሴ 19, 2021

    ወደ ማረፊያ ቤት ተዛወረ

  4. ሚያዝያ 29, 2022

    ‘የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አስተባብረሃል፣ ተሳትፎ አድርገሃል እንዲሁም ሌሎችን መልምለሃል’ የሚል ክስ በይፋ ተመሠረተበት

  5. ሰኔ 10, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a b ይህ ርዕስ በተጠናቀረበት ወቅት ወንድም ሱቮሮቭ ማረፊያ ቤት በመሆኑ የግል አስተያየቱን ማግኘት አልተቻለም።