ኅዳር 5, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | ወንድም አሌክሲ የርሾቭ መንፈሳዊ ልማዱ ለተስፋ መቁረጥ እጅ እንዳይሰጥ ረድቶታል
ሚያዝያ 7, 2022 የቶምስክ ክልል ፍርድ ቤት፣ ቀደም ሲል በወንድም አሌክሲ የርሾቭ ላይ የተበየነውን ፍርድ ወደ ሦስት ዓመት የገደብ እስራት ለውጦታል። አሌክሲ ወዲያውኑ ከእስር ተለቅቋል።
ጥር 19, 2022 በቶምስክ ክልል የሚገኘው የሴቬርስኪ ከተማ ፍርድ ቤት አሌክሲ ጥፋተኛ ነው በማለት የሦስት ዓመት እስራት ፈረደበት። ፍርዱ ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናል።
የክሱ ሂደት
ሰኔ 22, 2021
ክሱ በቶምስክ ክልል ለሚገኘው የሴቬርስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ቀረበ
መጋቢት 30, 2021
አሌክሲ ክስ ተመሠረተበት፤ አንድ ሰው ከአንድ ዓመት በላይ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፍላጎት ያለው መስሎ በመቅረብ የቀረጻቸው ቪዲዮዎች ለክሱ ማስረጃ ሆነው ቀርበዋል
ሐምሌ 14, 2020
የሩሲያ የደህንነት ሠራተኞችና የወንጀል ምርመራ ኮሚቴ አባላት የአሌክሲን ቤት ሰብረው በመግባት ለሰባት ሰዓት ያህል ብርበራ አካሂደዋል። ፖሊሶቹ የባንክ ደብተሮች፣ ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ፓስፖርቶችና የዋይ ፋይ ራውተሮች ወስደዋል
አጭር መግለጫ
በሩሲያ ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበባቸውና መጸለያቸው ወደፊትም ብርታት እንደሚሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም። መዝሙር 9:9 እንዲህ የሚል ማረጋገጫ ይሰጠናል፦ “ይሖዋ ለተጨቆኑ አስተማማኝ መጠጊያ ይሆናል፤ በመከራ ጊዜ አስተማማኝ መጠጊያ ነው።”