በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አናቶሊ ጎርቡኖቭ እና ባለቤቱ ገሊና

ነሐሴ 5, 2021
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም አናቶሊ ጎርቡኖቭ ሳያሰልስ መጸለዩ ደስታውን እንዲጠብቅ ረድቶታል

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም አናቶሊ ጎርቡኖቭ ሳያሰልስ መጸለዩ ደስታውን እንዲጠብቅ ረድቶታል

ሰኔ 21, 2022 የክራስናያርስክ ክልል ፍርድ ቤት የወንድም አናቶሊ ጎርቡኖቭን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ቀደም ሲል የተላለፈበትን የጥፋተኝነት ብይን አጽንቷል። በቅርቡ ከማረፊያ ቤት ወደ ወህኒ እንደሚዛወር ይጠበቃል።

የካቲት 2, 2022 በክራስናያርስክ የሚገኘው የኦክትያቢርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም አናቶሊ ጎርቡኖቭ ጥፋተኛ ነው በማለት የስድስት ዓመት እስራት ፈርዶበታል። ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስዷል።

የክሱ ሂደት

  1. የካቲት 9, 2021

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  2. መስከረም 15, 2020

    የአናቶሊ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተሸ። ፖሊሶቹ የቤቱን ቁልፎች ወሰዱ

  3. መጋቢት 25, 2020

    በአናቶሊ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ። እገዳ የተጣለበትን ድርጅት ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች በማደራጀት “ወንጀል” ተከሰሰ

  4. ኅዳር 7, 2018

    የአናቶሊ ቤት በማለዳ ተፈተሸ። ፖሊሶች ላፕቶፕ፣ ታብሌት፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ እና ሁለት ስልኮች ወረሱ። አናቶሊ ወደ ሩሲያ ፌዴሬሽን የምርመራ ኮሚቴ ቢሮ ተወስዶ ለአንድ ሰዓት ምርመራ ከተካሄደበት በኋላ ተለቀቀ

አጭር መግለጫ

አናቶሊና ቤተሰቡ አጥብቀው በመጸለይ በይሖዋ እንደሚታመኑ አሳይተዋል፤ እሱም እንደሚደግፋቸውና ደስታቸውን ለመጠበቅ እንደሚረዳቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 25:1, 2