በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አንድሬ ሌድያኪን

ኅዳር 18, 2021
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም አንድሬ ሌድያኪን ከይሖዋና ከእምነት አጋሮቹ ጋር የመሠረተው ወዳጅነት አጠናክሮታል

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም አንድሬ ሌድያኪን ከይሖዋና ከእምነት አጋሮቹ ጋር የመሠረተው ወዳጅነት አጠናክሮታል

ሚያዝያ 26, 2022 በቶምስክ ክልል የሚገኘው የሴቨርስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም አንድሬ ሌድያኪን ጥፋተኛ ነው በማለት የ26 ወር እስራት በየነበት። ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስዷል።

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 12, 2021

    የአንድሬ ክስ መታየት ጀመረ

  2. መጋቢት 30, 2021

    አንድሬ በጽንፈኝነት እንቅስቃሴ ተሳትፈሃል የሚል ክስ ተመሠረተበት

  3. መጋቢት 29, 2021

    አንድሬ የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  4. መጋቢት 25, 2021

    አንድሬ የወንጀል ክስ ፋይል ተከፈተበት። ይህን ተከትሎም ከሥራው ተባረረ

  5. ሐምሌ 14, 2020

    አንድሬ ሥራ ቦታው እያለ የፌዴራል ደህንነት አባላትና ሌሎች ሁለት ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር አዋሉት። በኋላ ላይ፣ ቤቱን ለ12 ሰዓታት ፈተሹ

  6. መጋቢት-ሚያዝያ 2020

    አንዲት የፌዴራል ደህንነት አባል፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የማወቅ ፍላጎት ያላት በመምሰል ከአንድሬ እንዲሁም ከሌሎች ወንድሞችና እህቶች ጋር ያደረገችውን ውይይት በድብቅ ትቀርጽ ነበር

አጭር መግለጫ

አንድሬ ብዙ ችግሮች ቢያጋጥሙትም “ልዩ በሆነ መንገድ” እንደተያዘ ማወቃችን ያበረታታናል።—መዝሙር 4:3