የካቲት 2, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | ወንድም አንድሬ ቭላሶቭ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች መጠመዱ አዎንታዊ እንዲሆን ረድቶታል
ሐምሌ 26, 2022 የኬሜሮቮ ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም አንድሬ ቭላሶቭ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል። ወንድም አንድሬ አሁንም እስር ቤት ነው።
ግንቦት 23, 2022 በፕሮኮፕዬቭስክ ከተማ ያለው የማዕከላዊ አውራጃ ፍርድ ቤትአንድሬ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን ያስተላለፈ ሲሆን የሰባት ዓመት እስራት ፈርዶበታል። ወንድም አንድሬ ወዲያውኑ ወህኒ ወርዷል።
የክሱ ሂደት
ሐምሌ 2, 2020
አንድሬ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴዎች በማደራጀት ተጠርጥሮ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት
ሐምሌ 12, 2020
የፌዴራል ደህንነት አባላት በአንድሬ ቤትና የሥራ ቦታ ላይ ፍተሻ አካሄዱ። የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችንና መጽሐፍ ቅዱሶችን ወረሱ። መርማሪዎች ባለቤቱን ናታሊያን ምርመራ ሲያካሂዱባት አንድሬ ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ
ሐምሌ 14, 2020
ከማረፊያ ቤት ተለቆ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
ሰኔ 9, 2021
ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ከአንድሬ እንዲሁም በሩሲያ እና በክራይሚያ ስደትን በደስታ እየተቋቋሙ ካሉት ሌሎች ወንድሞችና እህቶች ጋር አብሮ መሥራት እንዴት ያለ ታላቅ መብት ነው!—2 ቆሮንቶስ 1:24