ኅዳር 24, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | ወንድም አንድሬ ኮሌስኒቼንኮ ተፈጥሮን በማየት ብርታት አግኝቷል
ሰኔ 30, 2022 የቶምስክ ክልላዊ ፍርድ ቤት በወንድም አንድሬ ኮሌስኒቼንኮ ላይ ተላልፎ የነበረው የአራት ዓመት እስራት ፍርድ፣ በአራት ዓመት የገደብ እስራት እንዲቀየር ወስኗል። ወንድም አንድሬ ወዲያውኑ ከወህኒ ተለቅቋል።
ጥር 19, 2022 በቶምስክ ክልል የሚገኘው የሴቬርስኪ ከተማ ፍርድ ቤት አንድሬ ጥፋተኛ ነው በማለት የአራት ዓመት እስራት ፈረደበት።
የክሱ ሂደት
ሐምሌ 7, 2021
ክሱ መታየት ጀመረ
ግንቦት 21, 2021
በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎች ላይ ተሳትፈሃል የሚል ክስ ተመሠረተበት
መጋቢት 25, 2021
አንድሬ በወንጀል ተከሰሰ
ሐምሌ 14, 2020
የፌደራል ደህንነት አባላት በሴቬርስክ ከተማ የሚገኙ አምስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን ፈተሹ፤ ከእነዚህ አንዱ የወንድም አንድሬ ኮሌስኒቼንኮ ቤት ነው
አጭር መግለጫ
ምንጊዜም በይሖዋ የሚታመኑት የሩሲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በተዉት ምሳሌ ላይ ስናሰላስል “የአምላክን ቃል ያለፍርሃት ለመናገር” ድፍረት እናገኛለን።—ፊልጵስዩስ 1:13, 14