በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተግራ፦ እህት ማሪና ቻፕሊኪና። በስተቀኝ፦ ወንድም ቫለሪ ማሌትስኮቭ እና ባለቤቱ ማሪና

ነሐሴ 18, 2022 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 19, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም እና እህት ታሰሩ | በይሖዋ መታመናቸው ስደትን እንዳይፈሩ ረድቷቸዋል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም እና እህት ታሰሩ | በይሖዋ መታመናቸው ስደትን እንዳይፈሩ ረድቷቸዋል

ታኅሣሥ 18, 2023 በኖቮሲቢርስክ ክልል የሚገኘው የኖቮሲቢርስክ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ቫለሪ ማሌትስኮቭ እና እህት ማሪና ቻፕሊኪና ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ቫለሪ የስድስት ዓመት እስራት የተፈረደበት ሲሆን ማሪና ደግሞ የአራት ዓመት እስራት ተፈርዶባታል። ሁለቱም ከፍርድ ቤት ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል።

የክሱ ሂደት

  1. 2018

    በይሖዋ ምሥክሮች ላይ እገዳ ከመጣሉ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን ያጠናና በስብሰባዎች ላይ ይገኝ የነበረ አንድ ሰው በኖቮሲቢርስክ ከሚገኙ የፌዴራል ደህንነት አባላት ጋር በመተባበር በስብሰባዎቹ ላይ ስለሚገኙት ሰዎች መረጃ መሰብሰብ ጀመረ

  2. ሚያዝያ 19, 2019

    ይህ ሰው የሰጠውን መረጃ መሠረት በማድረግ በኖቮሲቢርስክ በሚኖሩ ስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ላይ ፍተሻ ተካሄደ። ቫለሪ ማሌትስኮቭ እና ማሪና ቻፕሊኪና ክስ ተመሠረተባቸው። ሁለቱም በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ማረፊያ ቤት እንዲገቡ ተደረገ

  3. ሚያዝያ 21, 2019

    ሁለቱም ከማረፊያ ቤት ተለቀቁ። ቫለሪ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ፤ ማሪና ቻፕሊኪና ደግሞ የጉዞ ገደብ ተጣለባት

  4. የካቲት 21, 2022

    ቫለሪ የጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎችን በማደራጀት ወንጀል ክስ ተመሠረተበት። ማሪና ቻፕሊኪና በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍና ለድርጅቱ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ወንጀል ተከሰሰች

  5. መጋቢት 30, 2022

    ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

የእምነት ባልንጀሮቻችን ስደትን በጽናት መጋፈጣቸው ይሖዋ እየባረካቸውና ጥበቃ እያደረገላቸው እንዳለ በግልጽ የሚያሳይ ነው።—1 ዮሐንስ 5:4