መጋቢት 9, 2022 | የታደሰው፦ ግንቦት 2, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ከክስ ነፃ ሆነ | ወንድም ኪሪል ጉሽቺን ለእምነት ባልንጀሮቹ መጸለዩ ብርታት ሰጥቶታል
ግንቦት 2, 2024 በካባርዲኖ ባልካሪያን ሪፑብሊክ የሚገኘው የማይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ኪሪል ጉሽቺን ጥፋተኛ አይደለም የሚል ውሳኔ አስተላልፏል። ከቀረቡበት ክሶች ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኗል።
የክሱ ሂደት
ግንቦት 20, 2020
መሣሪያ የታጠቁና ጭምብል ያጠለቁ የፌዴራል ደህንነት አባላት ኪሪል ወደ ሥራ እየሄደ ሳለ አስቆሙት። ፖሊሶቹ በካቴና ካሰሩት በኋላ ወደ ቤቱ ይዘውት ሄዱ። ቤታቸው እየተፈተሸ በነበረበት ወቅት እሱና ባለቤቱ ስቬትላና አንድ ክፍል ውስጥ እንዲቆዩ ተደረጉ። አንድ ፖሊሲ በባልና ሚስቱ መኝታ ቤት እና በአንድ ሌላ ክፍል ውስጥ የታገዱ ጽሑፎችን በስውር አስቀመጠ
ሚያዝያ 26, 2021
ባለሥልጣናቱ በድብቅ ስብሰባዎችን የቀዳ አንድ ሰው የሰጠውን ምሥክርነት መሠረት በማድረግ በኪሪል ላይ የወንጀል ክስ መሠረቱበት። መርማሪው፣ ኪሪል እንደዘመረና እንደጸለየ እንዲሁም በ1 ቆሮንቶስ 13:8 ላይ ስለሚገኘው “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል” የሚል ምክር ማብራሪያ እንደሰጠ በመግለጽ ከሰሰው።
ሚያዝያ 28, 2021
ባለሥልጣናቱ ኪሪልን ከሰሱት። በስቬትላና እና በሌሎች አራት እህቶች ላይ ሌላ የወንጀል ክስ ተመሠረተ
ግንቦት 19, 2021
በክሱ ከተካፈሉት የፌዴራል ደህንነት አባላት አንዱ፣ ምሥክሮችን በማስፈራራት ወንጀል ተከሰሰ፤ ይህ ሰው ከዚህ ቀደም በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የሐሰት ማስረጃ በማቅረብ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቶ ነበር። የምርመራ ዲፓርትመንቱ ኃላፊ ክሱ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አቃቤ ሕጉ እንዲመለስ ትእዛዝ ሰጠ
ሰኔ 7, 2021
ክሱ በድጋሚ ተመሥርቶ በማይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
እኛም ይሖዋ ለኪሪልም ሆነ በሩሲያና በክራይሚያ ስደት እየደረሰባቸው ላሉ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ “በመከራ ጊዜ አስተማማኝ መጠጊያ” እንደሚሆንላቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 9:9, 10