በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዬቭጌኒ ኮሮቱን

ኅዳር 25, 2021
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ዬቭጌኒ ኮሮቱን ከይሖዋ ማጽናኛ አግኝቷል

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ዬቭጌኒ ኮሮቱን ከይሖዋ ማጽናኛ አግኝቷል

ግንቦት 16, 2022 የቶምስክ ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ዬቭጌኒ ኮሮቱን ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል። አሁንም እስር ቤት ነው።

ጥር 20, 2022 በቶምስክ ክልል የሚገኘው የሴቬርስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ዬቭጌኒ ጥፋተኛ ነው በማለት የሰባት ዓመት እስራት ፈረደበት። ፍርዱ ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናል።

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 31, 2021

    ክሱ መታየት ጀመረ

  2. መስከረም 7, 2020

    በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋለ፤ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ ማረፊያ ቤት እንዲቆይ ተደረገ

  3. ሐምሌ 15, 2020

    የቁም እስረኛ ተደረገ

  4. ሐምሌ 14, 2020

    የፌደራል ደህንነት አባላት በሴቬርስክ ከተማ የሚገኙ አራት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን ፈተሹ፤ ከእነዚህ አንዱ የወንድም ዬቭጌኒ ኮሮቱን ቤት ነው

  5. ሐምሌ 13, 2020

    ዬቭጌኒ በወንጀል ተከሰሰ

  6. 2018–2019

    ሁለት የስውር ፖሊሶች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የማወቅ ፍላጎት ያላቸው መስለው ከዬቭጌኒ ጋር ያደረጉትን ውይይት በድብቅ ይቀርጹ ነበር፤ ይህን ያደረጉት ለክስ ማስረጃ ሆኖ እንዲያገለግላቸው ነው

አጭር መግለጫ

ይሖዋ የዬቭጌኒን ቤተሰብም ሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚያገለግሉትን በሙሉ እንደማይተዋቸው እርግጠኞች ነን።—ሮም 15:5

a ወንድም ዬቭጌኒ ኮሮቱን አሁን ማረፊያ ቤት ስለሆነ እሱ የሚሰጠውን ሐሳብ ማካተት አልቻልንም።