ነሐሴ 5, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ዲሚትሪ ቴሬቢሎቭ ለአምስተኛ ጊዜ ሊታሰር ይችላል፤ በእምነቱ ምክንያት ሲከሰስ ግን ይህ የመጀመሪያው ነው
መስከረም 22, 2022 አራተኛው ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ወንድም ዲሚትሪ ቴሬቢሎቭ ለሁለተኛ ጊዜ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። ዲሚትሪ አሁንም እስር ቤት ነው።
ጥር 12, 2022 የኮስትሮማ ክልላዊ ፍርድ ቤት የዲሚትሪን ይግባኝ ውድቅ አደረገ።
የክሱ ሂደት
መስከረም 6, 2021
በኮስትሮማ ከተማ የሚገኘው የስቬርድሎቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በዲሚትሪ ላይ የሦስት ዓመት እስራት ፈረደበት። ዲሚትሪ ብይኑ ከተላለፈ በኋላ ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወሰደ
መስከረም 8, 2020
የዲሚትሪ ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ግንቦት 25, 2020
ዲሚትሪ ተከሰሰ፤ እንዲሁም የጉዞ ገደብ ተጣለበት
መስከረም 19, 2019
የዲሚትሪ የባንክ ሒሳብ ታገደ
ሰኔ 13, 2019
ዲሚትሪ የታገዱ ጽሑፎችን በማሰራጨትና የታገደ ድርጅት ስብሰባዎችን በማደራጀት ወንጀል ክስ ተመሠረተበት
ሐምሌ 25, 2018
ዲሚትሪና ባለቤቱ በሞልዶቫ የክልል ስብሰባ ላይ ተገኝተው እየተመለሱ ሳሉ ቤታቸው ተፈተሸ። ዲሚትሪና ባለቤቱ ቤታቸው እንደደረሱ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ሥር አውለው ምርመራ አደረጉባቸው
አጭር መግለጫ
ዲሚትሪ ‘ለክርስቶስ ስም ሲል በመነቀፉ ደስተኛ ነው’፤ እኛም ‘የክብር መንፈስ ይኸውም የአምላክ መንፈስ በእሱ ላይ እንደሚያርፍ’ እርግጠኞች ነን።—1 ጴጥሮስ 4:14