በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ፕዮትር ክሩፕኖቭ እና ባለቤቱ ማያ

ጥር 4, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ፕዮትር ክሩፕኖቭ እና ባለቤቱ ማያ አስቀድመው መዘጋጀታቸውና ተስፋቸው ላይ ማተኮራቸው ረድቷቸዋል

ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ፕዮትር ክሩፕኖቭ እና ባለቤቱ ማያ አስቀድመው መዘጋጀታቸውና ተስፋቸው ላይ ማተኮራቸው ረድቷቸዋል

መጋቢት 9, 2022 የፔንዛ ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ፕዮትር ክሩፕኖቭ እና ባለቤቱ ማያ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።

የክሱ ሂደት

  1. ታኅሣሥ 30, 2021

    በፔንዛ ክልል የሚገኘው የኒኮልስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ፕዮትር እና ባለቤቱ ማያ ጥፋተኛ ናቸው በማለት በሦስት ዓመት የገደብ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

  2. ጥቅምት 25, 2021

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  3. ጥቅምት 12, 2021

    ፕዮትር እና ማያ ከወዳጆቻቸው ጋር ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስለተወያዩ በአሸባሪዎችና በጽንፈኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

  4. መስከረም 15, 2021

    በማያ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተባት። በኋላ ፕዮትርም በክሱ ውስጥ ተካተተ

  5. ጥቅምት 11, 2020

    የደህንነት አባላት የፕዮትርንና የማያን ቤት ጨምሮ የአራት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች በረበሩ

አጭር መግለጫ

ፕዮትር እና ማያ ተስፋቸውን አጽንተው በመያዝና በይሖዋ በመታመን ረገድ የተዉትን ምሳሌ ከልብ እናደንቃለን።—ዕብራውያን 6:19