ጥቅምት 1, 2021 | የታደሰው፦ ነሐሴ 29, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ተፈረደባቸው | አምስት ወንድሞች ስደት ቢደርስባቸውም ለመጽናት ቆርጠዋል
ነሐሴ 28, 2023 በኦረንበርግ የሚገኘው የፕሮሚሽሌኒ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ቭላዲሚር ኮችኔቭ፣ በወንድም ቭላዲስላቭ ኮልባኖቭ፣ በወንድም ፓቬል ሌኮንትሴቭ፣ በወንድም ሰርጌ ሎጉኖቭ እና በወንድም ኒኮላይ ዡጊን ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ወንድሞች ከሁለት ዓመት ተኩል እስከ ሦስት ዓመት ተኩል የሚደርስ የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።
የክሱ ሂደት
መጋቢት 1, 2021
ክሱ ወደ አቃቤ ሕግ ቢሮ ከተመለሰ ከአንድ ዓመት በላይ ካለፈ በኋላ ጉዳያቸው በኦረንበርግ በሚገኘው ፕሮሚሽሌኒ አውራጃ ፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ጥር 14, 2020
ክሱ በግልጽ ባለመቀመጡ የተነሳ ወደ አቃቤ ሕግ ቢሮ ተመለሰ
ነሐሴ 3, 2018
ቭላዲሚር በማረፊያ ቤት 79 ቀናት ካሳለፈ በኋላ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
ግንቦት 16, 2018
ባለሥልጣናቱ በኦረንበርግ ክልል የሚኖሩ 19 ቤተሰቦችን ቤት ፈተሹ። ቭላዲሚርን እና ቭላዲስላቭን ማረፊያ ቤት አስገቧቸው። ከሦስት ቀናት በኋላ ቭላዲስላቭ ከማረፊያ ቤት ተለቆ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
ግንቦት 14, 2018
በኦረንበርግ ክልል የሚገኘው የሩሲያ ፌዴሬሽን የምርመራ ኮሚቴ በአምስቱም ወንድሞች ላይ ክስ መሠረተ
አጭር መግለጫ
ወንድሞቻችን በእምነታቸው ምክንያት ክስ ከተመሠረተባቸው ከሦስት ዓመት የሚበልጥ ጊዜ ቢያልፍም እነዚህ ወንድሞች ለይሖዋ ታማኝ ሆነው ለመቀጠል እንደቆረጡ ምንም አያሻማም። ይሖዋም ለእነሱ ታማኝ እንደሆነ በግልጽ ማየት ይቻላል።—2 ሳሙኤል 22:26