በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም አሌክሳንደር ፖሎዞቭ እና ባለቤቱ ስቬትላና እንዲሁም ወንድም ስቴፓን ሼቬሌቭ እና ባለቤቱ ኦክሳና

ጥር 24, 2022 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 29, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ተፈረደባቸው | ወንድም አሌክሳንደር ፖሎዞቭ እና ወንድም ስቴፓን ሼቬሌቭ ስደት ቢደርስባቸውም በእጅጉ ተባርከዋል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ተፈረደባቸው | ወንድም አሌክሳንደር ፖሎዞቭ እና ወንድም ስቴፓን ሼቬሌቭ ስደት ቢደርስባቸውም በእጅጉ ተባርከዋል

ታኅሣሥ 29, 2023 በክራስናያርስክ ክልል የሚገኘው የኖሪልስክ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም አሌክሳንደር ፖሎዞቭ እና ወንድም ስቴፓን ሼቬሌቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ውሳኔ አሳልፏል። ሁለቱም የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 20, 2019

    ልዩ ኃይሎች በኖሪልስክ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝን አንድ የድንኳን መትከያ ቦታ ከበቡ። ከ50 በላይ የይሖዋ ምሥክሮች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

  2. ጥቅምት 26, 2019

    አሌክሳንደር ተይዞ ማረፊያ ቤት ገባ

  3. ጥር 21, 2020

    አሌክሳንደር ከሦስት ወር ገደማ በኋላ ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ

  4. የካቲት 19, 2020

    አሌክሳንደር በጽንፈኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ፤ የባንክ ሒሳቦቹም ታገዱ

  5. ግንቦት 6, 2021

    ስቴፓን ከአሌክሳንደር ጋር “በወንጀል ሴራ በመተባበር” ተከሰሰ። ስቴፓን ከተከሰሰባቸው “ወንጀሎች” መካከል መጸለይና መስበክ ይገኙበታል

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ስደት ቢደርስባቸውም በታማኝነት ጽድቅን ‘እያሳደዱ’ ያሉትን ውድ ወንድሞቻችንን መደገፉን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—መሳፍንት 8:4