በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ሮማን ማርዬቭ፣ ወንድም አናቶሊ ማሩኖቭ እንዲሁም ወንድም ሰርጌ ቶሎኮኒኮቭ እና ባለቤቱ ማሪያ

የካቲት 10, 2023 | የታደሰው፦ ሐምሌ 14, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ሦስት ወንድሞች ሞስኮ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ሦስት ወንድሞች ሞስኮ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሐምሌ 12, 2023 በሞስኮ የሚገኘው የሳቭዮሎቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ሮማን ማርዬቭ፣ ወንድም አናቶሊ ማሩኖቭ እና ወንድም ሰርጌ ቶሎኮኒኮቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሮማን የአራት ዓመት ከስድስት ወር፣ አናቶሊ የስድስት ዓመት ከስድስት ወር፣ ሰርጌ ደግሞ የአምስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። አናቶሊ ከፍርድ ቤት ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስዷል። ሮማን እና ሰርጌ ቀድሞውንም ማረፊያ ቤት ነበሩ።።

አጭር መግለጫ

ሮማን፣ አናቶሊ እና ሰርጌ ሊኮረጅ የሚገባ ግሩም ምሳሌ ትተውልናል። ምንም ዓይነት ችግር ቢገጥመን ይሖዋ ከእኛ ጋር እንዳለ ስለምናውቅ ‘ጉዳት ይደርስብናል ብለን አንፈራም።’—መዝሙር 23:4

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 20, 2021

    ባለሥልጣናት ሞስኮ ውስጥ ስምንት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን ፈተሹ። ሮማን፣ አናቶሊ እና ሰርጌ ‘የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አስተባብረዋል፤ ሌሎችም በእንቅስቃሴው እንዲሳተፉ ቀስቅሰዋል’ በሚል የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው። ሦስቱም ወንድሞች ጣቢያ እንዲቆዩ ተደረገ

  2. ጥቅምት 22, 2021

    ሮማን እና ሰርጌ ማረፊያ ቤት ተላኩ። አናቶሊ የቁም እስረኛ ተደረገ

  3. ሰኔ 17, 2022

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት ወንድም ሰርጌ ማረፊያ ቤት ነበር፤ በመሆኑም የእሱን አስተያየት ማግኘት አልተቻለም።