ታኅሣሥ 14, 2023 | የታደሰው፦ ጥር 30, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | “ቁልፉ በይሖዋ መታመን ነው”
ጥር 25, 2024በሳማራ የሚገኘው የሳማርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም አራም ዳኒዬልያን፣ ወንድም ዴኒስ ኩዝያኒን፣ ወንድም ሰርጌ ፖሎሴንኮ እና ወንድም ኒኮላይ ቫሲሊዬቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። እያንዳንዳቸው የሰባት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ከፍርድ ቤት ወዲያውኑ ወደ ወህኒ ተወስደዋል።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ በእምነታቸው ምክንያት ስደት እየደረሰባቸው ያሉትን ሁሉ ማጽናናቱን በመቀጠል ‘መልካም የሆነውን ነገር እንዲያደርጉና እንዲናገሩ እንደሚያጸናቸው’ ሙሉ እምነት አለን።—2 ተሰሎንቄ 2:16, 17
የክሱ ሂደት
ታኅሣሥ 14, 2021
በዴኒስ፣ በኒኮላይ እና በሰርጌ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ
ታኅሣሥ 15, 2021
የዴኒስ፣ የኒኮላይ እና የሰርጌ ቤት ተፈተሸ። በቁጥጥር ሥር ውለው ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ተወሰዱ
ታኅሣሥ 16, 2021
ዴኒስ፣ ኒኮላይ እና ሰርጌ ወደ ማረፊያ ቤት ተዛወሩ
ጥር 6, 2022
በአራም ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ። አየር መንገድ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ጥር 7, 2022
አራም ማረፊያ ቤት ገባ
ታኅሣሥ 12-14, 2022
አራቱም ወንድሞች ከማረፊያ ቤት ተለቀው የጉዞ ገደብ ተጣለባቸው
ሰኔ 16, 2023
ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ