መጋቢት 29, 2023 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 18, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | በእስር ላይ እያሉ የይሖዋን ድጋፍ ማግኘት
ሚያዝያ 17, 2023 በአስትራካን ክልል የሚገኘው የአክቱቢንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ሪናት ኪራሞቭ፣ ወንድም ሰርጌ ኮሮልዮቭ እና ወንድም ሰርጌ ኮስያኔንኮ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። እያንዳንዳቸው የሰባት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ሦስቱም ወንድሞች ከኅዳር 2021 ጀምሮ ማረፊያ ቤት የነበሩ ሲሆን እስራታቸው በዚሁ ይቀጥላል።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ ለታማኝ አገልጋዮቹ ምንጊዜም መሸሸጊያ እንደሚሆን ማወቃችን ያጽናናናል፤ ‘ዘላለማዊ ክንዶቹን ከእነሱ በታች’ በማድረግ ይንከባከባቸዋል።—ዘዳግም 33:27
የክሱ ሂደት
ኅዳር 9, 2021
የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው። ባለሥልጣናቱ በአኽቱቢንስክ እና በዝናምንስክ የሚገኙ 15 የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች ፈተሹ፤ ቤታቸው ከተፈተሸባቸው መካከል ወንድም ሪናት ኪራሞቭ፣ ወንድም ሰርጌ ኮሮልዮቭ እና ወንድም ሰርጌ ኮስያኔንኮ ይገኙበታል
ኅዳር 10, 2021
ሰርጌ ኮሮልዮቭ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ኅዳር 11, 2021
ሪናት ኪራሞቭ እና ሰርጌ ኮስያኔንኮ በቁጥጥር ሥር ዋሉ። ሦስቱም ወንድሞች ማረፊያ ቤት ወረዱ
ኅዳር 14, 2022
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ