በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከቀኝ ወደ ግራ፦ ሰርጌ አፋናሲዬቭ፣ አንቶን ኦልሼቭስኪ፣ አዳም ስቫሪኬቭስኪ እና ሰርጌ የርሚሎቭ

ግንቦት 18, 2022 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 21, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ተስፋ ወንድሞቻችን እንዲጸኑ ረድቷቸዋል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ተስፋ ወንድሞቻችን እንዲጸኑ ረድቷቸዋል

በአሙር ክልል የሚገኘው የብላጎቭዬሸዬንስኪይ ከተማ ፍርድ ቤት በወንድም ሰርጌ አፋናሲዬቭ፣ ሰርጌ ካርዳኮቭ፣ a አንቶን ኦልሼቭስኪ፣ አዳም ስቫሪኬቭስኪ እና ሰርጌ የርሚሎቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ወንድም አፋናሲዬቭ ስድስት ዓመት ከአምስት ወር እስራት ተፈርዶበታል። ወንድም ካርዳኮቭ ስድስት ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈርዶበታል። ወንድም ኦልሼቭስኪ፣ ስቫሪኬቭስኪ እና የርሚሎቭ ደግሞ ስድስት ዓመት ከሦስት ወር እስራት ተፈርዶባቸዋል። ወንድሞች ከፍርድ ቤት በቀጥታ ወህኒ ቤት ወርደዋል።

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 20, 2018

    ፖሊሶች የወንድም አፋናሲዬቭን፣ የወንድም ኦልሼቭስኪንና የወንድም ስቫሪኬቭስኪን ቤቶች ፈተሹ

  2. ጥቅምት 21, 2019

    በወንድም የርሚሎቭና በወንድም ኦልሼቭስኪ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ፤ ወንድሞች የተከሰሱት ባለሥልጣናቱ “ማኅበረሰቡን አደጋ ላይ ይጥላሉ” ባሏቸው ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች ላይ በመካፈላቸው ነው

  3. መስከረም 10, 2020

    በወንድም ስቫሪኬቭስኪ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። ክስ የተመሠረተበት ‘ከወንድም ኦልሼቭስኪና ከወንድም የርሚሎቭ ጋር እገዳ በተጣለበት ድርጅት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ተካፍለሃል’ በሚል ነው

  4. መስከረም 18, 2020

    ወንድም አፋናሲዬቭ በክስ ፋይሉ ላይ ተካተተ

  5. መስከረም 24, 2020

    የወንድም ካርዳኮቭ ቤት ተፈተሸ። በእሱም ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። የተከሰሰው ‘ለሕገ መንግሥቱና ለብሔራዊ ደህንነት መሠረት ለሆኑ እሴቶች ንቀት አሳይተሃል’ በሚል ወንጀል ነው፤ ይህ ክስ የተመሠረተበት መጽሐፍ ቅዱስን በማንበቡና ወደ ይሖዋ በመጸለዩ ነው

  6. መጋቢት 12, 2021

    ወንድም ኦልሼቭስኪ ‘የተከለከሉ ሃይማኖታዊ ስብሰባዎችን አስተባብሯል እንዲሁም የስብከት እንቅስቃሴዎችን መርቷል’ የሚል ተጨማሪ ክስ ተመሠረተበት

  7. ጥቅምት 21, 2021

    ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ለሁላችንም ግሩም ምሳሌ የሚሆኑ እነዚህ ወንድሞቻችን፣ ትኩረታቸው ያረፈው ዛሬ እየደረሰባቸው ባለው ጊዜያዊ መከራ ላይ ሳይሆን ይሖዋ በእሱ ለሚታመኑት አገልጋዮቹ ባዘጋጀው ዘላለማዊ ሽልማት ላይ ነው።—2 ቆሮንቶስ 4:17, 18

a b የወንድም ሰርጌ ካርዳኮቭን ፎቶግራፍና የግል አስተያየት እንዲሁም የወንድም አንቶን ኦልሼቭስኪን የግል አስተያየት ማግኘት አልተቻለም።