ኅዳር 30, 2022 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 29, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ክርስቲያናዊ ባሕርያትን እንዲያዳብሩ ረድቷቸዋል
በአሙር ክልል የሚገኘው የዜይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ዬቭጌኒ ቢቱሶቭ እና በወንድም ሊዮኒድ ድሩዢኒን ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ወንድም ቢቱሶቭ የስድስት ዓመት፣ ወንድም ድሩዢኒን ደግሞ የስድስት ዓመት ተኩል እስራት ተፈርዶባቸዋል። ብይኑ እንደተላለፈ ከፍርድ ቤት ወደ ወህኒ ወርደዋል።
አጭር መግለጫ
ስለ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ስናስብ ኩራት ይሰማናል፤ ምክንያቱም በጽናትና በትዕግሥት ብቁ የአምላክ አገልጋዮች መሆናቸውን እያስመሠከሩ ነው።—2 ቆሮንቶስ 6:3-10
የክሱ ሂደት
መጋቢት 21, 2019
የሕግ አስከባሪ አካላት፣ ዜያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች ፈተሹ፤ የዬቭጌኒና የሊዮኒድ ቤትም ተፈተሸ
ነሐሴ 10, 2020
የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው
ጥቅምት 13, 2020
የሕግ አስከባሪ አካላት፣ የዬቭጌኒንና የሊዮኒድን ቤት ድጋሚ ፈተሹ። ሊዮኒድ ወደ ጣቢያ ተወስዶ ለሁለት ሰዓት ምርመራ ተደረገበት
ሰኔ 20, 2022
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ