በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከላይ፣ ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ኒኮላይ ማርቲኖቭ፣ ሰርጌ ኮስቴዬቭ፣ ያሮስላቭ ካሊን እና ሚካኼል ሞይሽ

ከታች፣ ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ኢጎር ፖፖቭ፣ ዴኒስ ሳራዣኮቭ፣ አሌክሲ ሶልኔችኒ፣ አንድሬ ቶልማቼቭ እና ሰርጌ ቫሲሊዬቭ

ታኅሣሥ 27, 2023 | የታደሰው፦ መጋቢት 6, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ወንድሞች የእስራት ጊዜ መራዘምም ሆነ የቁም እስር አዎንታዊ አመለካከታቸውን አልነጠቃቸውም

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ወንድሞች የእስራት ጊዜ መራዘምም ሆነ የቁም እስር አዎንታዊ አመለካከታቸውን አልነጠቃቸውም

መጋቢት 5, 2024 በኢርኩትስክ የሚገኘው የኦክትያቢርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ኒኮላይ ማርቲኖቭ፣ ሰርጌ ኮስቴዬቭ፣ ያሮስላቭ ካሊን፣ ሚካኼል ሞይሽ፣ ኢጎር ፖፖቭ፣ ዴኒስ ሳራዣኮቭ፣ አሌክሲ ሶልኔችኒ፣ አንድሬ ቶልማቼቭ እና ሰርጌ ቫሲሊዬቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ፍርድ አስተላልፏል። ኒኮላይ፣ ሰርጌ ኮስቴዬቭ፣ ያሮስላቭ፣ ሚካኼል፣ አሌክሲ እና አንድሬ የሰባት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ኢጎር እና ዴኒስ የስድስት ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈርዶባቸዋል። ሰርጌ ቫሲሊዬቭ ደግሞ የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት ወዲያውኑ ከፍርድ ቤት ወደ ማረሚያ ቤት ተወስዷል። ሌሎቹ ወንድሞች ማረፊያ ቤት የነበሩ ሲሆን እስራታቸው በዚሁ ይቀጥላል።

አጭር መግለጫ

ውድ ወንድሞቻችን ለጊዜውም ቢሆን ከቤተሰቦቻቸው መለየት ግድ ሆኖባቸዋል፤ እስከጸኑ ድረስ ግን ከአምላክ ፍቅር ሊለያቸው የሚችል አንዳች ነገር እንደሌለ እርግጠኞች ነን።​—ሮም 8:35-39

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 4, 2021

    በኢርኩትስክ ክልል የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች ቤታቸው ተፈተሸ። ኒኮላይ፣ ሰርጌ ኮስቴዬቭ፣ ያሮስላቭ፣ ሚካኼል፣ አሌክሲ፣ አንድሬ እና ሰርጌ ቫሲሊዬቭ የክስ ፋይል ተከፈተባቸው። ሰባቱም ወንድሞች ወደ ጣቢያ ተወሰዱ

  2. ጥቅምት 5, 2021

    ያሮስላቭ፣ ሚካኼል እና አሌክሲ ማረፊያ ቤት ተላኩ

  3. ጥቅምት 6, 2021

    ሰርጌ ኮስቴዬቭ፣ ኒኮላይ እና አንድሬ ማረፊያ ቤት ተላኩ። ሰርጌ ቫሲሊዬቭ ከጣቢያ ተለቅቆ በቁም እስር እንዲቆይ ተወሰነ

  4. ኅዳር 30, 2021

    ተጨማሪ ቤቶች ተፈተሹ። ዴኒስ እና ኢጎር ተይዘው ከ1500 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ ወደሚገኘው ወደ ኢርኩትስክ ተወሰዱ

  5. ታኅሣሥ 1, 2021

    ኢጎር ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ

  6. ታኅሣሥ 2, 2021

    ዴኒስ ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ

  7. ታኅሣሥ 29, 2022

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a b c d e f ወንድም ኒኮላይ፣ ያሮስላቭ፣ ሚካኼል፣ ኢጎር፣ ዴኒስ እና አሌክሲ ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት ማረፊያ ቤት ስለነበሩ ቃለ መጠይቅ ልናደርግላቸው አልቻልንም።