ግንቦት 20, 2022 | የታደሰው፦ ጥቅምት 17, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች እስር ተፈረደባቸው | ቤተሰቦች በይሖዋ እገዛ ስደትን በጽናት እየተቋቋሙ ነው
ጥቅምት 13, 2023 በኦርዮል ከተማ የሚገኘው የሶቪየትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ቭላድሚር ሜልኒክ፣ ወንድም ቭላድሚር ፒስካሬቭ እና ወንድም አርተር ፑቲንሴቭ ጥፋተኞች ናቸው በማለት በእያንዳንዳቸው ላይ የስድስት ዓመት እስራት ፍርድ አስተላልፏል። ሦስቱም ወንድሞች ከታኅሣሥ 2020 ጀምሮ ማረፊያ ቤት የነበሩ ሲሆን አሁንም ወህኒ ይቆያሉ።
የክሱ ሂደት
ታኅሣሥ 8, 2020
በወንድም ሜልኒክ፣ በወንድም ፒስካሬቭ እና በወንድም ፑቲንሴቭ ላይ ክስ ተመሠረተ
ታኅሣሥ 9, 2020
ፖሊሶች በኦርዮል የሚገኙ ስምንት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች ፈተሹ፤ ከእነዚህ መካከል የሦስቱ ወንድሞች ቤቶች ይገኙበታል። በኋላም ወደ ጣቢያ ተወሰዱ
ታኅሣሥ 11, 2020
ወንድም ሜልኒክ እና ወንድም ፒስካሬቭ ማረፊያ ቤት እንዲገቡ ተደረገ
ታኅሣሥ 14, 2020
ወንድም ፑቲንሴቭ ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ
ጥር 19, 2021
ወንድም ፒስካሬቭ አስቸኳይ ክትትል የሚፈልጉ የጤና እክሎች እንዳሉበት ለባለሥልጣናቱ ተነገራቸው፤ ሆኖም አስፈላጊውን ሕክምናም ሆነ መድኃኒት እንዳያገኝ ከለከሉት
ጥር 21, 2021
ወንድም ፒስካሬቭ ባለቤቱ ያመጣችለትን መድኃኒት እንዲቀበል ተፈቀደለት፤ የሕክምና ክትትል ለማድረግ ግን አልተፈቀደለትም
ሰኔ 24, 2021
ወንድም ፒስካሬቭ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ተወሰደ፤ ስትሮክ እንዳጋጠመው ታወቀ። ይህ የጤና ችግር እንዳጋጠመው እየታወቀም ወደ ማረፊያ ቤት እንዲመለስ ተደረገ
ጥቅምት 29, 2021
ወንድሞች ‘ጽንፈኛ ተብሎ የተፈረጀን ድርጅት እንቅስቃሴዎች አስተባብረዋል’ የሚል ክስ ተመሠረተባቸው
ጥር 31, 2022
ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
እነዚህ ቤተሰቦች ለጊዜው መለያየት ግድ ሆኖባቸዋል፤ ከይሖዋ ፍቅራዊ እንክብካቤና ጥበቃ ሊለያቸው የሚችል አንዳች ነገር እንደሌለ ማወቃችን ግን ያጽናናናል።—ሮም 8:38, 39