መጋቢት 27, 2024 | የታደሰው፦ ግንቦት 13, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ጥፋተኛ ተባሉ | ልበ ሙሉ፣ ዝግጁና አዎንታዊ ሆኖ መጽናት
ግንቦት 13, 2024 በአልታይ ግዛት፣ በባርናውል ከተማ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ዩሪ ኮሎቲንስኪ፣ በወንድም ሚካይል ሬሼትኒኮቭ እና በወንድም አናቶሊ ሳሪቼቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሦስቱም የሁለት ዓመት ከሦስት ወር የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይገቡም።
አጭር መግለጫ
በይሖዋ ላይ እምነት በመጣልና በእሱ በመመካት ረገድ ግሩም ምሳሌ የሚሆኑ እንዲህ ያሉ ወንድሞች ስላሉን አመስጋኞች ነን። የይሖዋ ታማኝ ፍቅርና እንክብካቤ እንደማይለያቸው ሙሉ እምነት አለን።—መዝሙር 25:10
የክሱ ሂደት
ግንቦት 25, 2021
ሚካይል የክስ ፋይል ተከፈተበት
ግንቦት 27, 2021
የሚካይል ቤት ተፈተሸ። እሱና አንቶኒና ምርመራ ተደረገባቸው። ሚካይል የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት
ጥቅምት 6, 2022
አናቶሊ እና ዩሪ የክስ ፋይል ተከፈተባቸው፤ ከዚያም ክሳቸው በሚካይል መዝገብ እንዲካተት ተደረገ
ጥቅምት 7, 2022
አናቶሊ እና ዩሪ የጉዞ ገደቦች ተጣሉባቸው
ጥር 19, 2023
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ