ኅዳር 15, 2022 | የታደሰው፦ ኅዳር 17, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—የገንዘብ መቀጮ ተጣለበት | ስደትን እየተጋፈጡ ካሉት ብርታት ማግኘት
ኅዳር 17, 2022 በክራስናያርስክ የሚገኘው የዠለዝኖዶሮዥኒ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ኢጎር ጉሴቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ኢጎር 600,000 ሩብል (9,907 የአሜሪካ ዶላር) የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍል ተወስኗል።
የክሱ ሂደት
ግንቦት 21, 2020
በወንድም ቪታሊ ሱኮቭ ላይ ከተመሠረተው ክስ ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምርመራ ተጠራ
የካቲት 17, 2022
የታገደ ሃይማኖታዊ ድርጅት እንቅስቃሴ አስተባብረሃል ተብሎ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት
ነሐሴ 23, 2022
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
እኛም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በተዉት የድፍረት ምሳሌ እንበረታታለን። በተጨማሪም “ምግባራቸው ያስገኘውን ውጤት በሚገባ በማጤን በእምነታቸው [ለመምሰል]” እንነሳሳለን።—ዕብራውያን 13:7