በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ዬቭጌኒ ግሪኔንኮ፣ ወንድም ሰርጌ ኮቤሌቭ እና እህት ስቬትላና ዬፍሬሞቫ

ግንቦት 19, 2022 | የታደሰው፦ የካቲት 6, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—የጥፋተኝነት ብይን | በእምነታቸው ምክንያት ችሎት ፊት የቆሙ የሌሶዛቮድስክ የይሖዋ ምሥክሮች

ወቅታዊ መረጃ—የጥፋተኝነት ብይን | በእምነታቸው ምክንያት ችሎት ፊት የቆሙ የሌሶዛቮድስክ የይሖዋ ምሥክሮች

የካቲት 3, 2023 በፕሪሞርይስ ክልል የሚገኘው የሌሶዛቮድስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ዬቭጌኒ ግሪኔንኮ፣ ወንድም ሰርጌ ኮቤሌቭ እና እህት ስቬትላና ዬፍሬሞቫ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ዬቭጌኒ እና ሰርጌ እያንዳንዳቸው የስድስት ዓመት የገደብ እስራት፣ ስቬትላና ደግሞ የሦስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 12, 2020

    ዬቭጌኒ “ጽንፈኛ” ተብሎ የተፈረጀን ድርጅት እንቅስቃሴዎች አስተባብሯል የሚል የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። የፌዴራል ደህንነት አባላት የዬቭጌኒን እና የሰርጌን ቤት እንዲፈትሹ ተላኩ። ሌሎች ፖሊሶች ደግሞ ሰርጌ ወደሚሠራበት ቦታ ሄደው ያዙት። ለአራት ሰዓታት ምርመራ ካደረጉበት በኋላ ተለቀቀ። ዬቭጌኒም ተይዞ ማረፊያ ቤት ተወሰደ

  2. ግንቦት 14, 2020

    ፍርድ ቤቱ፣ ዬቭጌኒ ማረፊያ ቤት እንዲቆይ ትእዛዝ ሰጠ

  3. ግንቦት 29, 2020

    ባለሥልጣናቱ፣ ዬቭጌኒን ስፓስክ ዳልኒ ውስጥ ወደሚገኝ ማረፊያ ቤት አዛወሩት

  4. ሐምሌ 8, 2020

    ዬቭጌኒ ከማረፊያ ቤት ወጥቶ የቁም እስረኛ እንዲሆን ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጠ

  5. የካቲት 6, 2021

    ዬቭጌኒ ከቁም እስር ተለቀቀ፤ ሆኖም አካባቢውን ለቆ እንዳይሄድ ታገደ

  6. መጋቢት 8, 2021

    ሰርጌ “ጽንፈኛ” ተብሎ የተፈረጀ ድርጅት ባካሄዳቸው እንቅስቃሴዎች ተሳትፏል የሚል ክስ ተመሠረተበት

  7. ሚያዝያ 6, 2021

    ስቬትላና ክሱ ላይ ተካተተች

አጭር መግለጫ

ታማኝ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘ወደ አምላክ መንግሥት ለመግባት ሲሉ በብዙ መከራ እያለፉ’ ነው፤ ይህ የድፍረት ምሳሌያቸው እኛንም ያበረታታናል።—የሐዋርያት ሥራ 14:22