በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ኩዝነትሶቭ

ግንቦት 5, 2022 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 26, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—የጥፋተኝነት ብይን ተላለፈበት | ይሖዋ ለሰርጌ ኩዝነትሶቭ ኃይል ሰጥቶታል

ወቅታዊ መረጃ—የጥፋተኝነት ብይን ተላለፈበት | ይሖዋ ለሰርጌ ኩዝነትሶቭ ኃይል ሰጥቶታል

ታኅሣሥ 22, 2022 በካባረቭስክ ክልል የሚገኘው የቭያዜምስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ሰርጌ ኩዝነትሶቭን ጥፋተኛ ነው በማለት ሁለት ዓመት ከአምስት ወር የገደብ እስራት በይኖበታል። በእርግጥ አሁን ወህኒ አይወርድም።

የክሱ ሂደት

  1. መስከረም 3, 2020

    የፌዴራል ደህንነት አባላት የሰርጌን ቤት ፈተሹ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች፣ ፍላሽ ዲስኮችና ጽሑፎች ወረሱ

  2. ሚያዝያ 2, 2021

    በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ። የባንክ ሒሳቡ ታገደ

  3. ኅዳር 9, 2021

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለስሙ ሲሉ የሚደርስባቸውን ስደት በጽናት እየተቋቋሙ ላሉት በሩሲያና በክራይሚያ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ኃይል እንደሚሰጣቸው እርግጠኞች ነን።—ራእይ 2:3