መስከረም 26, 2022 | የታደሰው፦ ጥር 16, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—የጥፋተኝነት ብይን ተላለፈበት | ጠንካራ መንፈሳዊነት ፍርሃትን ለማሸነፍ ይረዳል
ጥር 12, 2023 በቱቫ ሪፑብሊክ የሚገኘው የክዝልስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም አናቶሊይ ስዬኒንን ጥፋተኛ ነው በማለት የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ፈርዶበታል። እርግጥ አሁን ወህኒ አይወርድም።
የክሱ ሂደት
ጥር 28, 2021
ቤቱ ከተፈተሸ በኋላ በቁጥጥር ሥር ውሎ ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ
ጥር 30, 2021
ከማረፊያ ቤት ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ
መጋቢት 27, 2021
ከቁም እስር ነፃ ሆነ፤ የጉዞ እገዳ ተጣለበት
ጥር 17, 2022
የይሖዋ ምሥክሮችን ሥራ በማደራጀት ወንጀል ተከሰሰ
ሚያዝያ 6, 2022
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የተናገረው “ልባችሁ አይረበሽ፤ በፍርሃትም አይዋጥ” የሚለው ሐሳብ ያጽናናናል።—ዮሐንስ 14:27