በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከላይ (ከግራ ወደ ቀኝ)፦ ወንድም አሌክሲ ዲያድኪን፣ ወንድም አሌክሲ ጎሬሊ እና ወንድም ኒኪታ ሞይሴዬቭ

ከታች (ከግራ ወደ ቀኝ)፦ ወንድም ቭላድሚር ፖፖቭ፣ ወንድም ዬቭጌኒ ራዙሞቭ እና ወንድም ኦሌግ ሺስሎቭስኪ

መጋቢት 24, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ይሖዋ በእስር ላይ የሚገኙ ስድስት ወንድሞችን ቤተሰቦች ተንከባክቧቸዋል

ወቅታዊ መረጃ | ይሖዋ በእስር ላይ የሚገኙ ስድስት ወንድሞችን ቤተሰቦች ተንከባክቧቸዋል

መስከረም 19, 2022 በሮስቶቭ ክልል የሚገኘው የጉኮቮ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ ዲያድኪን፣ ወንድም አሌክሲ ጎሬሊ፣ ወንድም ኒኪታ ሞይሴዬቭ፣ ወንድም ቭላድሚር ፖፖቭ፣ ወንድም ዬቭጌኒ ራዙሞቭ እና ወንድም ኦሌግ ሺድሎቭስኪ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ወንድም አሌክሲ ጎሬሊ እና ወንድም ኦሌግ ሺድሎቭስኪ የስድስት ዓመት ተኩል እስራት ተፈርዶባቸዋል። ወንድም አሌክሲ ዲያድኪን፣ ኒኪታ ሞይሴዬቭ፣ ወንድም ቭላድሚር ፖፖቭ እና ወንድም ዬቭጌኒ ራዙሞቭ ደግሞ የሰባት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ወንድሞች ወዲያውኑ ወህኒ ወርደዋል።

የክሱ ሂደት

  1. ነሐሴ 8, 2020

    የፌዴራል ደህንነት አባላት በሮስቶቭ ክልል በሚገኙ ሦስት ከተሞችና በኩርስክ ከተማ የሚገኙ 17 የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች ፈትሸዋል። ወንድም ጎሬሊ፣ ወንድም ሞይሴዬቭ፣ ወንድም ራዙሞቭ እና ወንድም ሺድሎብስኪ ተይዘው በማግስቱ ማረፊያ ቤት እንዲገቡ ተደረገ። ወንድም ፖፖቭ በፊዴራል መንግሥት ከሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተካተተ

  2. ነሐሴ 12, 2020

    የፌዴራል ደህንነት አባላት ወንድም ፖፖቭን በቁጥጥር ሥር አዋሉት። ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ

  3. ነሐሴ 21, 2020

    ወንድም ዲያድኪን ምርመራ ከተደረገበት በኋላ ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ

  4. ሰኔ 28, 2021

    አንድ ጠበቃ ስድስቱን ወንድሞች ለማነጋገር ወደ ማረፊያ ቤቱ መጣ። ወንድሞች በታሰሩበት ክፍል ያለው ሙቀት እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ እንደሚደርስ፣ ግድግዳው ሻጋታ እንዳለውና እስረኞች በኮቪድ-19 እየተያዙ እንደሆነ እንዲሁም ሌሎች ችግሮች እንዳሉ ለጠበቃው ነገሩት

  5. ሐምሌ 21, 2021

    ወንድም ፖፖቭ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዘ ችግር ስላጋጠመው በሌላ ማረፊያ ቤት ወደሚገኝ የሕክምና ክፍል ተላከ። ከጊዜ በኋላ ወደ ሆስፒታል ተወሰደ

  6. መስከረም 30, 2021

    ወንድም ፖፖቭ ከሁለት ወር በላይ ለሚሆን ጊዜ ሆስፒታል ተኝቶ ሕክምናውን ሲከታተል ከቆየ በኋላ ወደ ማረፊያ ቤት እንዲመለስ ተደረገ

  7. ኅዳር 17, 2021

    ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። ስድስቱም ወንድሞች በማረፊያ ቤት የሚቆዩበት ጊዜ ተራዘመ

አጭር መግለጫ

ይሖዋ እነዚህን ወንድሞችና ቤተሰቦቻቸውን እንዲረዳቸው መጸለያችንን እንቀጥላለን። ይሖዋ የሚያስፈልጋቸውን እምነትና ብርታት እንደሚሰጣቸው እንተማመናለን።—ሮም 15:30

a b c d e f ስድስቱም ወንድሞች ያሉት በማረፊያ ቤት ውስጥ ስለሆነ እነሱን ማነጋገር አልተቻለም።