በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ እህት ኢሪና ሲዶሮቫ፣ እህት ማትሪዮና ስፒሪያዲ እና ወንድም አሌክሳንደር ቭዬርጉኖቭ

ታኅሣሥ 28, 2021
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ይሖዋ እንደሚደግፋቸው ሙሉ እምነት ያላቸው ታማኝ የይሖዋ ምሥክሮች

ወቅታዊ መረጃ | ይሖዋ እንደሚደግፋቸው ሙሉ እምነት ያላቸው ታማኝ የይሖዋ ምሥክሮች

ሚያዝያ 4, 2022 በካካሲያ ሪፑብሊክ የምትገኘው የአባካን ከተማ ፍርድ ቤት እህት ማትሪዮና ስፒሪያዲ እና ወንድም አሌክሳንደር ቭዬርጉኖቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሁለቱም የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። የሚያሳዝነው ተመሳሳይ ክስ ተመሥርቶባት የነበረችው እህት ኢሪና ሲዶሮቫ ሕይወቷ አልፏል። እርግጥ ማትሪዮና እና አሌክሳንደር አሁን ወህኒ አይወርዱም።

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 30, 2021

    የደህንነት ሠራተኞች የማትሪዮናን እና የአሌክሳንደርን ቤት ፈተሹ

  2. ሐምሌ 17, 2020

    ኢሪና ከቀዶ ሕክምና በኋላ ባጋጠማት ችግር ምክንያት ሕይወቷ አለፈ

  3. ግንቦት 20, 2020

    ባለሥልጣናት ኢሪና በጽንፈኝነት እንቅስቃሴ ተካፍላለች ብለው ስለጠረጠሩ ምርመራ አደረጉባት

  4. ግንቦት 19, 2020

    ባለሥልጣናት አሌክሳንደር በጽንፈኝነት እንቅስቃሴ ተካፍሏል ብለው ስለጠረጠሩ ምርመራ አደረጉበት

  5. ሚያዝያ 20, 2020

    በአሌክሳንደር፣ በኢሪና እና በማትሪዮና ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

አጭር መግለጫ

አምላካችን ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን በሙሉ እንደሚመለከታቸውና እንደሚያደንቃቸው እርግጠኞች ነን። እነዚህን ውድ አገልጋዮቹን መንከባከቡን እንደማያቋርጥ ሙሉ እምነት አለን።—ኢሳይያስ 49:15