ጥቅምት 27, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ይግባኙ ውድቅ ሆነ | “ይሖዋ ጠባቂዬ ሆኖልኛል”
ኅዳር 1, 2022 የፕሪሞርይስ ክልል ፍርድ ቤት የእህት ሊያ ማልትሴቫን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።
መስከረም 20, 2022 በፕሪሞርይስ ክልል የሚገኘው የፓርቲዛንስክ ከተማ ፍርድ ቤት ሊያ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል። እህት ሊያ የሁለት ዓመት ከሦስት ወር የገደብ እስራት ተበይኖባታል።
የክሱ ሂደት
ሰኔ 22, 2021
የሊያ ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ነሐሴ 18, 2020
የሩሲያ ደህንነት (የሩሲያ የሚስጥር ፖሊስ) አባላት የሊያን ቤት ከፈተሹ በኋላ በርካታ መጽሐፍ ቅዱሶችን፣ የማመሣከሪያ መጻሕፍትን እና ስልኳን ወረሱ። ከዚያም ወደ ወንጀል ምርመራ ዲፓርትመንት ለምርመራ ተወሰደች
ሐምሌ 9, 2020
የሩሲያ ፌዴሬሽን የገንዘብ ዝውውር ቁጥጥር አገልግሎት ሊያን በአሸባሪዎችና በጽንፈኞች ዝርዝር ውስጥ አካተታት
ሰኔ 1, 2020
በሩሲያ ፌዴሬሽን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት በሊያ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተባት። እገዳ የተጣለበት ሃይማኖታዊ ድርጅት በሚያካሂዳቸው እንቅስቃሴዎች በመካፈል ወንጀል ተከሰሰች
አጭር መግለጫ
ሊያ ባሳየችው ጽናት ተበረታተናል፤ ይሖዋ ለታማኝነቷ እንደሚባርካት ሙሉ በሙሉ እንተማመናለን።—1 ሳሙኤል 26:23