መስከረም 23, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ይግባኙ ውድቅ ተደረገ | ስድስት እህቶችና አንድ ወንድም ክስ ቢመሠረትባቸውም እንኳ በይሖዋ እና በወንድሞቻቸው ታምነዋል
መስከረም 26, 2022 የፕሪሞርይስ ክልላዊ ፍርድ ቤት እህት ናዴዥዳ አኖይኪና፣ እህት ልዩቦቭ ጋላክቲዮኖቫ፣ እህት ናይልያ ኮጋይ፣ እህት ኒና ፑርጌ፣ እህት ራይሳ ኡሳኖቫ እና ወንድም ቫለንቲን ኦሳድቹክ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።
ሰኔ 1, 2022 በቭላዲቮስቶክ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ናዴዥዳ፣ ልዩቦቭ፣ ናይልያ፣ ኒና፣ ራይሳ እና ቫለንቲን ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሁሉም እህቶች የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። ቫለንቲን ደግሞ የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖበታል። እርግጥ አሁን እስር ቤት አይገቡም። የ87 ዓመት አረጋዊት የሆኑት እህት የሌና ዛይሹክ በጠና ስለታመሙ ክሳቸው ለጊዜው ተቋርጧል።
የክሱ ሂደት
ጥር 19, 2021
ክሱ በቭላዲቮስቶክ ወደሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ተመራ
ኅዳር 12, 2019
ክሱ ወደ አቃቤ ሕግ ቢሮ ተመለሰ
ሚያዝያ 5, 2019
በዚህ ክስ ውስጥ የተካተተው ብቸኛ ወንድም ማለትም ቫለንቲን ከ274 ቀን የማረፊያ ቤት ቆይታ በኋላ ተለቀቀ። ከዚያም በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
ሚያዝያ 19, 2018
የፌዴራል ደህንነት አባላት የሰባቱን የይሖዋ ምሥክሮች ቤት በረበሩ
ሚያዝያ 9, 2018
የፕሪሞርስኪ ክልል የፌዴራል ደህንነት ቢሮ የወንጀል ምርመራ ክፍል በቫለንቲን እና በስድስቱ እህቶች ላይ ክስ መሠረተ
አጭር መግለጫ
በሩሲያ ያሉ ውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ምሳሌ ምንጊዜም ያበረታታናል። በሕይወት የሚያኖር እምነት እንዳላቸው እያሳዩ ነው።—ዕብራውያን 10:39