በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ልዩድሚላ ሼኮልዲና

መጋቢት 4, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ይግባኙ ውድቅ ተደረገ | እህት ልዩድሚላ ሼኮልዲና ያገኘችው ማበረታቻ ብርቱ አድርጓታል

ወቅታዊ መረጃ—ይግባኙ ውድቅ ተደረገ | እህት ልዩድሚላ ሼኮልዲና ያገኘችው ማበረታቻ ብርቱ አድርጓታል

ጥቅምት 6, 2022 የክራስኖዳር ክልል ፍርድ ቤት እህት ልዩድሚላ ሼኮልዲና ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል። ልዩድሚላ እንደታሰረች ትቆያለች።

ግንቦት 23, 2022 በክራስኖዳር ክልል የሚገኘው የፓቭሎቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ልዩድሚላ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን ያስተላለፈ ሲሆን የአራት ዓመት ከአንድ ወር እስራት ፈርዶባታል። ልዩድሚላ ወዲያውኑ ወህኒ ወርዳለች።

የክሱ ሂደት

  1. ሚያዝያ 23, 2020

    ከአንድ ሰላይ ጋር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በመወያየቷ በወንጀል ተከሰሰች

  2. ሚያዝያ 29, 2020

    ፖሊሶች ለዘጠኝ ሰዓታት የልዩድሚላን ቤት የፈተሹ ሲሆን በእሷም ላይ ምርመራ አካሂደውባታል። የጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎችን በማስፋፋት ወንጀል ክስ ተመሠረተባት

  3. ሰኔ 21, 2021

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ልዩድሚላን ጨምሮ ስደት እየደረሰባቸው ያሉ ታማኝ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በይሖዋ እርዳታ ብርቱዎች ሆነው እንደሚጸኑ እንተማመናለን።—መዝሙር 68:28