ታኅሣሥ 30, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ይግባኙ ውድቅ ተደረገ | ወንድም ኒኮላዬቭ በይሖዋ ላይ ያለው እምነት ውስጣዊ ሰላሙን ጠብቆ እንዲቀጥል ረድቶታል
ጥቅምት 20, 2022 የክራስኖዳር ግዛት ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሳንደር ኒኮላዬቭ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል። አሌክሳንደር እስር ቤት ይቆያል።
የክሱ ሂደት
ታኅሣሥ 23, 2021
በክራስኖዳር ክልል የሚገኘው የአብንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት አሌክሳንደር ጥፋተኛ ነው በማለት በሁለት ዓመት ተኩል እስራት እንዲቀጣ ወሰነ
መስከረም 30, 2021
ማረፊያ ቤት ገባ
ነሐሴ 4, 2021
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ግንቦት 26, 2021
ከቤተሰቡና ከወዳጆቹ ጋር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ተወያይቷል በሚል ወንጀል ተከሰሰ፤ መርማሪዎቹ ይህን ድርጊት “በሕገ መንግሥታዊው ሥርዓትና በአገሪቱ ደህንነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል” እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩታል
ሚያዝያ 7, 2021
ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ የደህንነት አባላትና ፖሊሶች ወንድም ኒኮላዬቭና ቤተሰቡ የሚኖሩበትን ቤት ፈተሹ። ወንድም ኒኮላዬቭ ለምርመራ የተወሰደ ሲሆን በኋላ ላይ ተለቀቀ
መጋቢት 31, 2021
በኒኮላዬቭ ላይ ክስ ተመሠረተበት
አጭር መግለጫ
ወንድም ኒኮላዬቭን ጨምሮ በሩሲያና በክራይሚያ ያሉ ታማኝ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በይሖዋ በመታመናቸው እንደሚባረኩ እርግጠኞች ነን።—ኤርምያስ 17:7