በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከላይ፣ በስተ ግራ፦ ወንድም ፕዮትር ፊሊዝኖቭ። ከታች፣ በስተ ግራ፦ ወንድም አንድሬ ቭዩሺን። በስተ ቀኝ፦ ወንድም አሌክሳንደር ኩዝኔትሶቭ እና ባለቤቱ ማሪያ

የካቲት 13, 2023 | የታደሰው፦ ኅዳር 6, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ይግባኝ | ስደት በያሮስላቭል የሚኖሩ ሦስት ቤተሰቦችን ቤት አንኳኳ

ወቅታዊ መረጃ—ይግባኝ | ስደት በያሮስላቭል የሚኖሩ ሦስት ቤተሰቦችን ቤት አንኳኳ

ጥቅምት 30, 2023 በያሮስላቭል የሚገኘው የዜርዢንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ፕዮትር ፊሊዝኖቭ እና ወንድም አንድሬ ቭዩሺን ያቀረቡትን ይግባኝ በከፊል ተቀብሎታል። የተላለፈባቸው የስድስት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ወደ ሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ተቀንሷል። የወንድም አሌክሳንደር ኩዝኔትሶቭ እና የባለቤቱ የማሪያ ብይን ግን በዚያው ይጸናል።

ነሐሴ 3, 2023 በያሮስላቭል የሚገኘው የዜርዢንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ፕዮትር ፊሊዝኖቭ፣ ወንድም አሌክሳንደር ኩዝኔትሶቭ እና ባለቤቱ እህት ማሪያ ኩዝኔትሶቫ እንዲሁም ወንድም አንድሬ ቭዩሺን ጥፋተኛ እንደሆኑ ወስኗል። በሁሉም ላይ የገደብ እስራት ፍርድ አስተላልፏል። አንድሬ እና ፕዮትር የስድስት ዓመት ተኩል፣ አሌክሳንደር እና ማሪያ ደግሞ የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

እንደ እነዚህ አራት ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች ሁሉ እኛም ‘በይሖዋ ከሚታመኑትና ፈጽሞ ከማይናወጡት’ አንዱ እንደምንሆን መተማመን እንችላለን።—መዝሙር 125:1

የክሱ ሂደት

  1. ሚያዝያ 13, 2021

    ቤታቸው በባለሥልጣናት ከተፈተሸ በኋላ ጣቢያ ተወሰዱ

  2. ሚያዝያ 15, 2021

    ወደ ማረፊያ ቤት ተላኩ

  3. ሐምሌ 14, 2021

    ከማረፊያ ቤት ተለቀቁ፤ ከዚያም የጉዞ ክልከላ ተጣለባቸው

  4. መስከረም 9, 2022

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ