ሰኔ 15, 2022 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 23, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ይግባኝ | ጋሊና ኮቤሌቫ ችሎት ፊት ምሥክርነት ለመስጠት ቆርጣለች
ታኅሣሥ 21, 2022 የፕሪሞርይስ ክልል ፍርድ ቤት፣ እህት ጋሊና ኮቤሌቫ ያቀረበችውን ይግባኝ በከፊል ተቀብሎታል። አሁን የፍርድ ቤት ወጪዋን ከራሷ መክፈል አይጠበቅባትም። የተላለፈባት የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ግን ይጸናል።
ጥቅምት 20, 2022 በፕሪሞርይስ ክልል የሚገኘው የሌሶዛቮድስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በእህት ጋሊና ኮቤሌቫ ላይ ብይን አስተላልፏል። ጋሊና የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባታል። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።
የክሱ ሂደት
ግንቦት 12, 2020
የፕሪሞርይስ ክልል የደህንነት አባላት የአራት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች በረበሩ፤ ከእነዚህ አንዱ የጋሊና ቤት ነው። ጋሊና እና ሰርጌ ኮቤሌቭ የተባለው ልጇ ለምርመራ ተጠሩ፤ ክትትል ይደረግባቸውም ጀመር
መጋቢት 8, 2021
ባለሥልጣናቱ በጋሊና ላይ ክስ መሠረቱ። የተከሰሰችበት ወንጀል ‘በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ ተሳትፋለች’ የሚል ነው
ሚያዝያ 7, 2021
የጉዞ እገዳ ተጣለባት
ጥቅምት 29, 2021
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ አምላካችን፣ እንደ ጋሊና ያሉ ለስሙ በድፍረት ጥብቅና የሚቆሙ ታማኝ አገልጋዮቹን “ደህንነት ወደሚገኝበት ስፍራ” እንደሚያመጣቸው በማወቃችን ምንኛ አመስጋኞች ነን።—2 ሳሙኤል 22:18-21