በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ጋሊና አብሮሲሞቫ

ግንቦት 10, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ጋሊና አብሮሲሞቫ ፍርሃቷን ማሸነፍ ችላለች

ወቅታዊ መረጃ | ጋሊና አብሮሲሞቫ ፍርሃቷን ማሸነፍ ችላለች

ነሐሴ 11, 2022 የኒዥኒ ኖቭጎሮድ ክልላዊ ፍርድ ቤት እህት ጋሊና አብሮሲሞቫ ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል። እርግጥ አሁን ወህኒ አትወርድም።

ግንቦት 6, 2022 በኒዥኒ ኖቭጎሮድ የሚገኘው የሶቪየትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ጋሊና ጥፋተኛ ነች በማለት የስድስት ዓመት የገደብ እስራት በየነባት።

የክሱ ሂደት

  1. ሰኔ 4, 2019

    መርማሪዎች በኒዥኒ ኖቭጎሮድ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ የይሖዋ ምሥክሮች ላይ ክስ መሠረቱ። ክሱ ‘ስብሰባ አድርገዋል፣ መዋጮ ሰብስበዋል እንዲሁም እገዳ የተጣለበትን ሃይማኖታዊ ድርጅት እንዲቀላቀሉ አዳዲስ አባላትን መልምለዋል’ የሚል ነው

  2. ሐምሌ 17, 2019

    በ35 የይሖዋ ምሥክር ቤተሰቦች ቤቶች ላይ የጅምላ ፍተሻ ተካሄደ። ጋሊና በቁጥጥር ሥር ውላ ለሁለት ቀናት ማረፊያ ቤት ቆየች

  3. ጥቅምት 19, 2021

    የጋሊና ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለሩሲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ቀርቦ ለእነሱ ለመመሥከር’ የሚያስችል ድፍረት እንደሚሰጣቸው እርግጠኞች ነን።—ማርቆስ 13:9