ነሐሴ 26, 2021 | የታደሰው፦ ጥር 12, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ፍርዱ ተቀለበሰ | የሁለት ልጆች አባት የሆነ ወንድም በእምነቱ ምክንያት የ15 ዓመት እስራት ሊፈረድበት ይችላል
ጥር 11, 2024 በሃንቲ ማንሲስክ ራስ ገዝ ክልል በዩግራ የሚገኘው ክልላዊ ፍርድ ቤት በወንድም አንድሬ ሳዞኖቭ ላይ የተላለፈው ብይን እንዲቀለበስ ወስኗል። ጉዳዩ በድጋሚ እንዲታይ በሃንቲ ማንሲስክ ራስ ገዝ ክልል በዩግራ ወደሚገኘው የኡራይ ከተማ ፍርድ ቤት ተመልሷል።
የክሱ ሂደት
ታኅሣሥ 24, 2021 በሃንቲ ማንሲስክ ራስ ገዝ ክልል በዩግራ የሚገኘው የኡራይ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም አንድሬ ሳዞኖቭ ወንጀለኛ ነው በማለት 500,000 ሩብል (6,785 የዩናይትድ ስቴትስ ዶላር) እንዲከፍል በይኖበታል። አንድሬ እስከ 15 ዓመት የሚደርስ እስራት ሊፈረድበት ይችል ነበር። ወንድማችን ወንጀለኛ ነው ተብሎ የተፈረደበት መሆኑ ቢያሳዝነንም እስር ቤት የማይገባ በመሆኑ ደስተኞች ነን
ሰኔ 22, 2020
የአንድሬ ክስ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ነሐሴ 22, 2019
ከቁም እስር ተለቀቀ፤ ፍርድ ቤቱ የጉዞ ገደብና ሌሎች እገዳዎች ጣለበት
የካቲት 26, 2019
በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
የካቲት 6, 2019
በቁጥጥር ሥር ዋለ፤ ከሁለት ቀናት በኋላ የሥራ ቦታውና መኪናው ከተፈተሸ በኋላ ወደ ማረፊያ ቤት ተወሰደ
ጥር 31, 2019
“የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴዎች በማደራጀትና በእንቅስቃሴዎቹ በመካፈል” ወንጀል ክስ ተመሠረተበት
አጭር መግለጫ
ስደቱ ቢቀጥልም በሩሲያ ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የተዉትን ግሩም ምሳሌ በጣም እናደንቃለን። ይሖዋ ምንጊዜም “ደፋርና ብርቱ” እንደሚያደርጋቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 138:3