በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ዬጎር ባራኖቭ እና ወንድም የን ሰን ሊ

ነሐሴ 13, 2021 | የታደሰው፦ መጋቢት 6, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ፍርዱ ተቀነሰለት | ወንድም ባራኖቭ እና ወንድም ሊ በይሖዋ በመተማመን ተረጋግተዋል

ወቅታዊ መረጃ—ፍርዱ ተቀነሰለት | ወንድም ባራኖቭ እና ወንድም ሊ በይሖዋ በመተማመን ተረጋግተዋል

መጋቢት 1, 2023 የካባረቭስክ ክልል ፍርድ ቤት፣ የወንድም ዬጎር ባራኖቭን ይግባኝ ከተመለከተ በኋላ የገደብ እስራቱ ወደ አራት ዓመት ከስድስት ወር እንዲቀነስ ወስኗል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

ሰኔ 6, 2022 በካባረቭስክ ክልል የሚገኘው የቭያዜምስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ዬጎር ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን ያስተላለፈ ሲሆን የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ፈርዶበታል። የሚያሳዝነው ወንድም የን ሰን ሊ የፍርድ ሂደቱ ከማብቃቱ በፊት ሕይወቱ አልፏል።

የክሱ ሂደት

  1. የካቲት 2, 2021

    የዬጎር እና የየን ሰን ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  2. ኅዳር 20, 2020

    ዬጎር ለ177 ቀናት በማረፊያ ቤት ከቆየ በኋላ ተለቀቀ

  3. ነሐሴ 26, 2020

    በካባረቭስክ የሚገኘው ማዕከላዊ አውራጃ ፍርድ ቤት የየን ሰንን መኪና ወረሰ

  4. ግንቦት 29, 2020

    ዬጎር ማረፊያ ቤት ገባ

  5. ግንቦት 26, 2020

    በካባረቭስክ ክልል በዬጎር እና በየን ሰን ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ

አጭር መግለጫ

ወንድሞቻችን በይሖዋ መተማመናቸውን በመቀጠላቸው እናደንቃቸዋለን፤ እሱም እንዲጸኑ እንደሚረዳቸው እንተማመናለን።—2 ተሰሎንቄ 3:3