በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ልዩድሚላ ሳሊኮቫ

ጥር 31, 2022 | የታደሰው፦ መጋቢት 27, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ፍርዱ ተቀነሰላት | እህት ልዩድሚላ ሳሊኮቫ ከይሖዋ ብርታትና ማጽናኛ አግኝታለች

ወቅታዊ መረጃ—ፍርዱ ተቀነሰላት | እህት ልዩድሚላ ሳሊኮቫ ከይሖዋ ብርታትና ማጽናኛ አግኝታለች

መጋቢት 23, 2023 የቼልያቢንስክ ክልላዊ ፍርድ ቤት እህት ልዩድሚላ ሳሊኮቫ ለሁለተኛ ጊዜ ያቀረበችውን ይግባኝ ሰምቶ ውሳኔ አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ፣ ቀደም ሲል የተፈረደባት የገደብ እስራት ከስድስት ዓመት ወደ ሁለት ዓመት ተኩል እንዲቀነስ ወስኗል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።

መጋቢት 17, 2022 የቼልያቢንስክ ክልላዊ ፍርድ ቤት ልዩድሚላ ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል።

ጥር 20, 2022 በቼልያቢንስክ ክልል የሚገኘው የስኔዢንስክ ከተማ ፍርድ ቤት ልዩድሚላ ጥፋተኛ ነች በማለት የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ፈረደባት።

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 2020

    በስኔዢንስክ የሚገኙ የደህንነት ኃይሎች ልዩድሚላን ጨምሮ የአራት የይሖዋ ምሥክር ቤተሰቦችን ቤቶች ፈተሹ። ፖሊሶች የሥራ ቦታዋንም ፈተሹ። በኋላም ሥራዋን ለመልቀቅ ተገደደች

  2. ነሐሴ 26, 2021

    ልዩድሚላ እገዳ የተጣለበትን ሃይማኖታዊ ድርጅት እንቅስቃሴ በማደራጀትና የታገዱ ጽሑፎችን ወደ አገሪቱ በማስገባት ወንጀል ተከሰሰች

  3. ታኅሣሥ 8, 2021

    ጉዳይዋ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

በሩሲያ ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከይሖዋ ብርታትና ማጽናኛ ማግኘታቸውን ቀጥለዋል። አፍቃሪው አምላካችን “በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ከእንግዲህ እንዳያሸብራቸው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለተደቆሱ ሰዎች ፍትሕ” እንደሚያሰፍን ዋስትና ሰጥቶናል።—መዝሙር 10:18