በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ፓቬል ብሪልኮቭ

ኅዳር 15, 2023 | የታደሰው፦ መጋቢት 13, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ፍርዱ ተቀየረ | ‘በይሖዋ ለመታመን ቁርጥ ውሳኔ አድርጌአለሁ’

ወቅታዊ መረጃ—ፍርዱ ተቀየረ | ‘በይሖዋ ለመታመን ቁርጥ ውሳኔ አድርጌአለሁ’

መጋቢት 12, 2024 የኬሜሮቮ ክልላዊ ፍርድ ቤት ይግባኙን ሰምቶ በወንድም ፓቬል ብሪልኮቭ ላይ የተላለፈውን ፍርድ ቀይሯል። መጀመሪያ ላይ ተፈርዶበት የነበረው የጉልበት ሥራ በሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተቀይሮለታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

ጥር 15, 2024 የፕሮኮፕዬቭስክ አውራጃ ማዕከላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ፓቬል ብሪልኮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ በማስተላለፍ ለሁለት ዓመት ከአሥር ወር ያህል የጉልበት ሥራ እንዲሠራ በይኖበታል። a በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

በውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የሚደርሰው ስደት ቢያሳዝነንም ‘የሚያድነንን አምላክ በትዕግሥት ለመጠባበቅ’ ቁርጥ ውሳኔ አድርገናል፤ ምክንያቱም እሱ የሰጣቸው ተስፋዎች እንደሚፈጸሙ እርግጠኞች ነን።—ሚክያስ 7:7

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 10, 2021

    ቤታቸው ተፈተሸ። ፓቬል እና ቬራ ምርመራ ተደረገባቸው

  2. ግንቦት 30, 2022

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  3. መጋቢት 16, 2023

    የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  4. ግንቦት 25, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a የጉልበት ሥራ እንዲሠራ የተበየነበት ሰው፣ ባለሥልጣናት የመደቡለትን ሥራ የሚያከናውን ሲሆን ከደሞዙ ከ5 እስከ 20 በመቶ የሚሆነው ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል። ባለሥልጣናቱ ግለሰቡ ለመተባበር ወይም የተሰጠውን ሥራ ለመሥራት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ከተሰማቸው ወህኒ እንዲወርድ ሊወስኑ ይችላሉ።