በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፣ ከላይ፦ ወንድም ሰርጌ አጋድዣኖቭ እንዲሁም እህት ልዩቦቭ አስትራያን፣ እህት ጋሊና ዴርጋቺዮቫ እና እህት ኢና ካርዳኮቫ

መሃል፦ እህት ኢሪና ኽቮስቶቫ እና እህት ጋሊና ፔችኮ እንዲሁም ወንድም ኮንስታንቲን ፔትሮቭ፣ ወንድም ኢቫን ፑይዳ እና ወንድም ቪክቶር ሬቭያኪን

ከታች፦ ወንድም ማይካዪል ሶልንትሴቭ እና ባለቤቱ ኦክሳና ሶልንትሴቫ እንዲሁም ወንድም ሰርጌ ዬርኪን እና ወንድም ዬቭጌኒ ዝያብሎቭ

ጥቅምት 17, 2022 | የታደሰው፦ መጋቢት 7, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ፍርድ ተላለፈባቸው | ማጋዳን ውስጥ አሥራ ሦስት የይሖዋ ምሥክሮች ለፍርድ ቀረቡ

ወቅታዊ መረጃ—ፍርድ ተላለፈባቸው | ማጋዳን ውስጥ አሥራ ሦስት የይሖዋ ምሥክሮች ለፍርድ ቀረቡ

መጋቢት 6, 2024በማጋዳን ክልል የሚገኘው የማጋዳን ከተማ ፍርድ ቤት የሚከተሉት ወንድሞችና እህቶች ጥፋተኛ ናቸው የሚል ፍርድ አስተላልፏል፦ ሰርጌ አጋድዣኖቭ፣ ልዩቦቭ አስትራያን፣ ጋሊና ዴርጋቺዮቫ፣ ኢና ካርዳኮቫ፣ ኢሪና ኽቮስቶቫ፣ ጋሊና ፔችኮ፣ ኮንስታንቲን ፔትሮቭ፣ ኢቫን ፑይዳ፣ ቪክቶር ሬቭያኪን፣ ማይካዪል ሶልንትሴቭ፣ ኦክሳና ሶልንትሴቫ፣ ሰርጌ ዬርኪን እና ዬቭጌኒ ዝያብሎቭ።

ሰርጌ አጋድዣኖቭ፣ ልዩቦቭ፣ ጋሊና ዴርጋቺዮቫ፣ ኢና፣ ኢሪና፣ ጋሊና ፔችኮ፣ ቪክቶር፣ ማይካዪል እና ኦክሳና የሦስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። ዬቭጌኒ የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖበታል። ኮንስታንቲን፣ ኢቫን እና ሰርጌ ዬርኪን ደግሞ የሰባት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። ሁሉም ወንድሞችና እህቶች በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 30, 2018

    ኢቫን፣ ኮንስታንቲን፣ ሰርጌ ዬርኪን እና ዬቭጌኒ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አስተባብራችኋል በሚል የወንጀል ምርመራ ይደረግባቸው ጀመር

  2. ሰኔ 1, 2018

    አራቱም ወንድሞች ማረፊያ ቤት ገቡ

  3. ነሐሴ 3, 2018

    ኮንስታንቲን ከማረፊያ ቤት ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ

  4. ጥቅምት 5, 2018

    ኢቫን፣ ሰርጌ ዬርኪን እና ዬቭጌኒ ከማረፊያ ቤት ተለቅቀው የቁም እስረኛ ተደረጉ

  5. መጋቢት 20, 2019

    ሰርጌ አጋድዣኖቭ፣ ጋሊና ዴርጋቺዮቫ፣ ኢና፣ ኢሪና፣ ልዩቦቭ፣ ማይካዪል፣ ኦክሳና እና ቪክቶር የወንጀል ምርመራ ይደረግባቸው ጀመር። ሁሉም የጉዞ እገዳ ተጣለባቸው

  6. መጋቢት 27, 2019

    ኢቫን፣ ኮንስታንቲን፣ ሰርጌ ዬርኪን እና ዬቭጌኒ ከቁም እስር ተፈቱ፤ የጉዞ እገዳ ተጣለባቸው

  7. ሚያዝያ 1, 2019

    የወንጀል ክሶቹ በአንድ መዝገብ ተያዙ

  8. መጋቢት 2, 2021

    ጋሊና ፔችኮ የጉዞ እገዳ ተጣለባት

  9. መጋቢት 5, 2021

    ጋሊና ፔችኮ በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎች ተሳትፋለች የሚል ክስ ቀረበባት፤ ክሷም በ12ቱ ወንድሞችና እህቶች መዝገብ ውስጥ ተካተተ

  10. ሚያዝያ 25, 2022

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

‘ለክርስቶስ ስም ሲሉ እየተነቀፉ’ ባሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ ‘የአምላክ መንፈስ እንደሚያርፍ’ እናውቃለን፤ ደስታቸውን ጠብቀው መጽናታቸውን ማየታችንም በእጅጉ ያበረታታናል።—1 ጴጥሮስ 4:14

a የወንድም ሰርጌ አጋድዣኖቭን ሐሳብ ማግኘት አልተቻለም።