በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ማክሲም ቤልቲኮቭ

መስከረም 24, 2021
ሩሲያ

ወንድም ማክሲም ቤልቲኮቭ አዘውትሮ በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች መካፈሉ ብርታት ሰጥቶታል

ወንድም ማክሲም ቤልቲኮቭ አዘውትሮ በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች መካፈሉ ብርታት ሰጥቶታል

ወቅታዊ መረጃ | የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ማክሲም ቤልቲኮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላለፈ

ጥር 17, 2022 በክራስኖዳር ክልል የሚገኘው የፓቭሎቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ማክሲም ቤልቲኮቭ ጥፋተኛ ነው በማለት የሁለት ዓመት እስራት በየነበት። በመሆኑም ወዲያውኑ እስር ቤት እንዲገባ ተደርጓል።

የክሱ ሂደት

  1. ሰኔ 29, 2020

    ከአካባቢው እንዳይወጣ እገዳ ተጣለበት

  2. ሰኔ 23, 2020

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። የተከሰሰው “በሃይማኖታዊ ትምህርት ፕሮግራም ላይ ተካፍሏል” በሚል ነው፤ ይህም “በሃይማኖታዊ ጽሑፎች ላይ የተመሠረቱ ንግግሮችን ማቅረብንና ማዳመጥን” ይጨምራል

  3. ሚያዝያ 29, 2020

    ባለሥልጣናቱ የማክሲምን ቤት ፈተሹ። በኋላም ማክሲም ምርመራ ተደረገበት

አጭር መግለጫ

በሩሲያ ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፣ አዘውትረው በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች በመካፈላቸው እንዲሁም ከሚወዷቸው ወንድሞቻቸው በሚያገኙት ድጋፍ እንዲበረታቱ እንመኛለን። “የፍቅርና የሰላም አምላክ” ከእነዚህ ውድ የእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር እንደሚሆን እርግጠኞች ነን።—2 ቆሮንቶስ 13:11