ጥቅምት 31, 2024
ሩሲያ
ወንድም ሮማን ማርዬቭ ከሩሲያ ወህኒ ቤት ተለቀቀ
ጥቅምት 25, 2024 ወንድም ሮማን ማርዬቭ ከእስር ተለቋል። ወንድም ሮማን ጥፋተኛ ነው በሚል የአራት ዓመት ከስድስት ወር እስራት የተፈረደበት ሐምሌ 12, 2023 ነበር። ማረፊያ ቤት ያሳለፈውን ወደ ሁለት ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ታሳቢ በማድረግ አሁን የእስር ጊዜው ተጠናቅቋል።
ሮማን ለመጽናት ብርታት የሆነው ምን እንደሆነ ክሱን ለተመለከተው ችሎት ሲያስረዳ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “እውነተኛ ደስታ ማግኘቴ በውጭያዊ ነገሮች ላይ የተመካ አይደለም። ደስተኛ የሆንኩት ትክክል የሆነውን ነገር በማድረጌ እንዲሁም ድርጊቴና በአምላክ መሥፈርቶች መመራቴ በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ስለሚያስገኝልኝ ነው። በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለኝ እርግጠኛ የሆንኩት ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ሮም 15:13 ‘በእሱ በመታመናችሁ የተነሳ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተስፋ እንዲትረፈረፍላችሁ ተስፋ የሚሰጠው አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ’ ይላል። ኢፍትሐዊ ሁኔታን ለመጋፈጥ ብገደድም ልቤ በደስታና በሰላም ተሞልቷል። አምላክ መንፈሱንና በረከቱን ባይሰጠኝ ኖሮ ይህ ሊሆን ይችል ነበር?”
ወንድም ሮማን ከቤተሰቡ ጋር በመቀላቀሉ ተደስተናል። ይሖዋ ታማኝነታችንን ለመጠበቅ የምናደርገውን ጥረት ምንጊዜም እንደሚባርክ ማወቃችንም አጽናንቶናል።—2 ዜና መዋዕል 15:7