የካቲት 26, 2021
ሩሲያ
ወንድም ሰርጌ ቨርክሆቱሮቭ የሰባት ዓመት እስራት ሊፈረድበት ቢችልም በአቋሙ እንደጸና ነው
የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን
በኒዥኒ ኖቭጎሮድ የሚገኘው የፕሪኦክስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት የወንድም ሰርጌ ቨርክሆቱሮቭን ጉዳይ ተመልክቶ ውሳኔ ለማሳለፍ መጋቢት 1, 2021 a ቀጠሮ ይዟል። ወንድም ሰርጌ ሰባት ዓመት ሊፈረድበት ይችላል።
አጭር መግለጫ
ሰርጌ ቨርክሆቱሮቭ
የትውልድ ዘመን፦ 1974 (ባይካልስክ፣ ኢርኩትስክ ክልል)
ግለ ታሪክ፦ ለአሥር ዓመት ያህል የኤሌክትሪክ ባለሙያ ሆኖ ሠርቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለአንድ ኩባንያ የሕግ አማካሪ ሆኖ እየሠራ ነው
ከልጅነቱ አንስቶ መጽሐፍ ቅዱስን የማወቅ ጉጉት ነበረው። ትልቅ ሰው ከሆነ በኋላ፣ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ጥናት የጀመረ የሥራ ባልደረባው የሚያሳየው መልካም ምግባር በጣም አስገረመው። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ተስማማ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ለመረዳት ቀላል እና አሳማኝ መሆኑ አስገረመው። በ1995 ተጠመቀ። በ2001 ከቪክቶሪያ ጋር ትዳር መሠረተ
የክሱ ሂደት
ሐምሌ 16 እና 17, 2019 የሩሲያ ባለሥልጣናት በኒዥኒ ኖቭጎሮድ ክልል የሚገኙ 35 የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች ፈተሹ። ከተፈተሹት መካከል የሰርጌ እና የቪክቶሪያ ቤትም ይገኝበታል። ሰርጌ፣ ፖሊሶች ቤቱን ስለበረበሩበት ወቅት ሲናገር “ተረጋግቼ ነበር፤ ብዙ አልተጨነቅኩም” ብሏል። ፖሊሶቹ ሚስጥራዊ የሆነ መረጃ ሊነግራቸው ፈቃደኛ ካልሆነ ቪክቶሪያን እንደሚያስሯት ዛቱበት። ሰርጌ “ይህ በጣም ከብዶኝ ነበር” ብሏል። ሰርጌ በይሖዋ እርዳታ መረጋጋት የቻለ ሲሆን ቪክቶሪያም b አልታሰረችም።
እንዲህ ብሏል፦ “ገና ስላልተፈጠሩ ነገሮች መፍራት እንደሌለብኝ ተምሬያለሁ፤ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ የፈራነው ላይደርስ ይችላል። በአንድ ፈተና ውስጥ በምትሆኑበት ጊዜ ፈተናው ከአቅም በላይ የሚመስለው ለሌሎች እንደሆነ ትገነዘባላችሁ። በፈተና ውስጥ ስታልፉ የይሖዋን ልዩ ድጋፍ እያገኛችሁ እንደሆነ ይሰማችኋል።”
ሰርጌ ደስታውን ጠብቆ ለመቀጠል ሲል ትኩረቱን በይሖዋ እና በሕዝቦቹ ላይ ያደርጋል። እንዲህ ብሏል፦ “ብቸኛው ፍላጎቴ ይሖዋ ስሙን ሲያስከብረው ማየት ነው። ስለዚህ ጉዳይ ስጸልይ ቆይቻለሁ፤ ወደፊትም መጸለዬን እቀጥላለሁ። በተጨማሪም ለይሖዋ ስም ክብር በሚያመጣና ለሌሎች ጥሩ ምሥክርነት በሚሰጥ መንገድ መጽናት እንድችል እጸልያለሁ። ከዚህ ስደት ጋር በተያያዘ ያጋጠሙኝ ሰዎች ስለ አምላክ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም፤ ስለ እሱ ያላቸው እውቀት በጣም ውስን ነው። ይሖዋ እሱን እንዲቀበሉ እንዲረዳቸው አጥብቄ እለምነዋለሁ።”
በሩሲያ የሚገኙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስደት እየደረሰባቸው ባለበት በዚህ ወቅት እኛም እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ “የሰላም ጌታ ራሱ በሁሉም መንገድ ዘወትር ሰላም ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን” እንላቸዋለን።—2 ተሰሎንቄ 3:16