በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ግሮሞቭ እና ባለቤቱ ዬሌና

መስከረም 15, 2023
ሩሲያ

ወንድም ሰርጌ ግሮሞቭ የስድስት ዓመት ከአንድ ወር እስራት ተፈረደበት

ወንድም ሰርጌ ግሮሞቭ የስድስት ዓመት ከአንድ ወር እስራት ተፈረደበት

መስከረም 14, 2023 በካዛን የሚገኘው የሞስኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ሰርጌ ግሮሞቭ ጥፋተኛ ነው በማለት የስድስት ዓመት ከአንድ ወር እስራት ፈረደበት። ከመጋቢት 15, 2022 ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን አሁንም በዚያው ይቆያል።

አጭር መግለጫ

ሰርጌና ዬሌና ላሳዩን የታማኝነትና በይሖዋ የመታመን ምሳሌ አመስጋኞች ነን። ታማኝ መሆናቸውና የይሖዋን በረከት ማግኘታቸው አንድ ሐቅ ያረጋግጥልናል፤ ይኸውም “የይሖዋ እጅ ማዳን ይሳናት ዘንድ አላጠረችም፤ ጆሮውም መስማት ይሳናት ዘንድ አልደነዘዘችም።”—ኢሳይያስ 59:1

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 15, 2022

    የክስ ፋይል ተከፈተበት። ለምርመራ ተወስዶ ጣቢያ እንዲቆይ ተደረገ

  2. መጋቢት 16, 2022

    ቤቱ ተፈተሸ

  3. መጋቢት 17, 2022

    ወደ ማረፊያ ቤት ተዛወረ

  4. መጋቢት 30, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  5. መስከረም 14, 2023

    ጥፋተኛ ነው ተብሎ የስድስት ዓመት ከአንድ ወር እስራት ተፈረደበት

a ይህ ዜና ሲጠናቀር ወንድም ሰርጌ ማረፊያ ቤት ስለነበር የእሱን አስተያየት ማግኘት አልተቻለም።