በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አንድሬ ስቱፕኒኮቭ (መሃል) ከቁም እስር ከተለቀቀ በኋላ ከወዳጆቹ ጋር ሆኖ

ሐምሌ 5, 2019
ሩሲያ

ወንድም ስቱፕኒኮቭ ከቁም እስር ተለቀቀ

ወንድም ስቱፕኒኮቭ ከቁም እስር ተለቀቀ

ሐምሌ 2, 2019 በክራስናያርስክ፣ ሩሲያ የሚገኝ ፍርድ ቤት ወንድም አንድሬ ስቱፕኒኮቭ ከቁም እስር እንዲለቀቅ ወሰነ። ወንድም ስቱፕኒኮቭ ከቁም እስር ቢለቀቅም ክሱ አልተዘጋም።

ወንድም አንድሬ ስቱፕኒኮቭ

ሐምሌ 3, 2018 ጠዋት ወንድም ስቱፕኒኮቭና ባለቤቱ በየሜሊያናቫ ሩሲያ ወደሚገኘው የክራስናያርስክ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እየገቡ ነበር። ሁለት የፌደራል ደህንነት አባላት ወንድም ስቱፕኒኮቭን በቁጥጥር ሥር አዋሉት። ከዚያም ያለፍርድ ለስምንት ወራት ከታሰረ በኋላ በ2019 የካቲት ወር መጨረሻ ላይ የቁም እስረኛ ሆነ።

ወንድም ስቱፕኒኮቭ እንደገለጸው ከሆነ ያለፈው ዓመት ራሱንና ከይሖዋ ጋር ያለውን ዝምድና እንዲመረምር አጋጣሚ ሰጥቶታል። እንዲህ ብሏል፦ “[እኔና ኦልጋ] የይሖዋ ምሥክሮች ከሆንን በርካታ ዓመታት ያለፉ ቢሆንም ከይሖዋ ጋር ያለን ዝምድና የአሁኑን ያህል የጠበቀ ሆኖ አያውቅም! በጣም አስቸጋሪ የሆነ ሁኔታ ባጋጠመኝ ጊዜ ሁሉ አባታችን ይሖዋ ሁሌም ከጎኔ እንደሆነና እንደሚደግፈኝ ይሰማኝ ነበር። ይሖዋ የቅርብ ወዳጄ ነበር፤ ለጸሎቴም ፈጣን ምላሽ ይሰጠኝ ነበር።”

ወንድም ስቱፕኒኮቭ እንዲህ ብሏል፦ “አባታችን ይሖዋ ስሜቴን እንደሚረዳ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ እርግጠኛ ሆኛለሁ። ያጋጠመኝ ነገር በእሱ ይበልጥ እንድታመንና ስለ ስደት ከመጠን በላይ እንዳልጨነቅ ረድቶኛል። ይበልጥ ሊያስፈራኝ የሚገባው ከይሖዋ ጋር ያለኝን ወዳጅነት ማጣት ነው። በእሱ ድጋፍ ማንኛውንም ፈተና ማሸነፍ እንደምችል እርግጠኛ ነኝ።”

እስከ ሐምሌ 1 ድረስ በሩሲያ በሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የተከፈቱት የወንጀል ክሶች 217 ደርሰዋል። የሩሲያ ባለሥልጣናት በአንዳንድ ወንድሞቻችን ላይ የጣሉትን ቅጣት የቀነሱበት ጊዜ አለ። ያም ቢሆን የምንታመነው በፍርድ ቤቶች ወይም በባለሥልጣናት ሳይሆን በይሖዋ ነው። ይሖዋ በሩሲያ የሚገኙ የእምነት ባልንጀሮቻችንን በሙሉ ማጠናከሩንና መጠበቁን እንዲቀጥል እንጸልያለን።—መዝሙር 28:7