በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ፦ ወንድም አሌክሳንደር ስክቮርትሶቭ። በስተ ቀኝ፦ ወንድም ቫለሪ ቲቢ

ሰኔ 27, 2023
ሩሲያ

ወንድም ስክቮርትሶቭ እና ወንድም ቲቢ ተፈረደባቸው

ወንድም ስክቮርትሶቭ እና ወንድም ቲቢ ተፈረደባቸው

ሰኔ 20, 2023 በሮስቶቭ ክልል የሚገኘው የታጋንሮግ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም አሌክሳንደር ስክቮርትሶቭ እና ወንድም ቫለሪ ቲቢ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። አሌክሳንደር የሰባት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። ከታኅሣሥ 7, 2021 ጀምሮ ማረፊያ ቤት ቆይቷል፤ አሁንም እንደታሰረ ይቀጥላል። ቫለሪ የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶበታል። ከግንቦት 18, 2022 ጀምሮ ማረፊያ ቤት የቆየ ሲሆን አሁን ተለቅቋል።

አጭር መግለጫ

ይሖዋን ለፍቅራዊ እንክብካቤውና ለሚሰጠን መመሪያ እናመሰግነዋለን፤ የሚያጋጥመንን ማንኛውንም ፈተና መወጣት የቻልነው በእሱ ነው።—መዝሙር 5:12

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 20, 2021

    የአሌክሳንደር ስክቮርትሶቭ ቤት ተፈተሸ

  2. ታኅሣሥ 7, 2021

    የአሌክሳንደር ስክቮርትሶቭ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተሸ፤ በዚህ ወቅት በታጋንሮግ ያሉ ሌሎች 29 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችም ተፈተሹ። አሌክሳንደር የወንጀል ክስ ተመሠረተበት፤ ጣቢያ እንዲቆይ ተደረገ

  3. ታኅሣሥ 8, 2021

    አሌክሳንደር ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ

  4. መጋቢት 29, 2022

    ቫለሪ የክስ ፋይል ተከፈተበት

  5. መጋቢት 31, 2022

    መርማሪዎቹ የአሌክሳንደርና የቫለሪ ጉዳይ በአንድ የክስ መዝገብ እንዲካተት ወሰኑ

  6. ግንቦት 18, 2022

    ቫለሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ ጣቢያ እንዲቆይ ተደረገ

  7. ግንቦት 26, 2022

    ቫለሪ ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ

  8. ታኅሣሥ 6, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  9. ሰኔ 20, 2023

    አሌክሳንደር የሰባት ዓመት እስራት ተፈረደበት። ቫለሪ የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደበት

a b ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት ወንድም አሌክሳንደር እና ወንድም ቫለሪ ማረፊያ ቤት ነበሩ፤ በመሆኑም የእነሱን አስተያየት ማግኘት አልተቻለም።