በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቫለሪ ባይሎ

ሐምሌ 22, 2024
ሩሲያ

ወንድም ቫለሪ ባይሎ እስራት ተፈረደበት

ወንድም ቫለሪ ባይሎ እስራት ተፈረደበት

ሐምሌ 3, 2024 በክርራስኖዳር ክልል የአቢንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ቫለሪ ባይሎ ጥፋተኛ ነው በማለት የሁለት ዓመት ከስድስት ወር እስራት ፈርዶበታል። በመሆኑም ወንድም ቫለሪ በእስር ላይ ይቆያል።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለቫለሪና በእስር ላይ ለሚገኙት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሁሉ “ዘላለማዊ ፍቅር” እንደሚያሳያቸውና ጥበቃው እንደማይለያቸው እርግጠኞች ነን።—​—ኤርምያስ 31:3

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 28, 2024

    የክስ ፋይል ተከፈተበት

  2. ሚያዝያ 2, 2024

    ምርመራ ተደረገበት እንዲሁም በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎች ላይ ተካፍሏል ተብሎ ተወነጀለ። ወደ ጣቢያ ተወሰደ

  3. ሚያዝያ 4, 2024

    ወደ ማረፊያ ቤት ተዛወረ

  4. ሰኔ 26, 2024

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  5. ሐምሌ 3, 2024

    ዳኛው የክሱን ሂደት በሦስት ቀጠሮዎች ብቻ ከተመለከቱ በኋላ ቫለሪ ጥፋተኛ ነው በማለት የሁለት ዓመት ከስድስት ወር እስራት ፈረዱበት።